2015 ሳፍሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ.

Days
Hours
Minutes
Seconds

ይህ ወድድር የኢትዮጲያ ሴት አትሌቶች በአቴንስ ኦሎምፒክ ላደረጉት አስተወጽኦ እንዲሁም አጠቃላይ ሴቶች በኢትዮጲያ ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ህይወት ላይ ያላቸውን ጉልህ ድርሻ ለማሳየት በ2004 እ.ኤ.አ. ቅድሚያ ለሴቶች በሚል መሪ ቃል ተጀመረ፡፡

ውድድሩ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ ከ100 ሺህ በላይ እድሜያቸው ከ5 እስከ 75 የሚሆኑ ሴቶች ተሳትፈዋል፡፡ በ2013 ዓ.ም. ሺህ ሴቶችን በማሳተፍ የተሳታፊዎች ቁጥር ተመዝግቧል፡፡ ይህም ውድድሩን ከኢትዮጵያ ትልቁ፣ ከአፍሪካ ደግሞ በተወዳዳሪ ብዛት ከታላላቆቹ የሴቶች ብቻ ሩጫዎች መካከል ያደርገዋል።

ይህ ውድድር በየአመቱ በሴቶች ዙሪያ የተለያዩ ማህበራዊ መልዕክቶችን ይዞ የሚካሄድ ሲሆን በ2013 “የኢትዮጲያ ሴቶች እናክብር” በሚል መሪቃል ውድድሩ ተካሂዷል

19ኛው ሳፍሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ሩጫ መጋቢት 04 ቀን 2014 ዓ.ም. ይካሄዳል።

ምዝገባው የፊታችን ሰኞ የካቲት 7 ቀን በ3 የእናት ባንክ ቅርንጫፎች ማለትም በካዛንችስ፤ በሚክሲኮ እና መገናኛ እንዲሁም በታላቁ ሩጫ ቢሮ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

ውጤት ለማየት እዚህ ይጫኑ