የህፃናት ሩጫ

Days
Hours
Minutes
Seconds

የ15ኛውን ዙር የፕሌይማተርስ የልጆች ሩጫ ውድድር ህዳር 10፣ 2015 ዓ.ም. ይካሄዳል

የውድድር ፕሮግራም

02:15 – 02:35 በአራት ምድቦች የተከፋፈለ የአካል ጉዳተኛ ልጆች ውድድር ይካሄዳል።

02:40 – 02:55 የሙዚቃና የዳንስ ዝግጅት ከመድረክ ይቀርባል።

02:45 – 03:50 በየ10 ደቂቃ ልዩነት ከ5፥8 እና ከ11 ዓመት በታች የወንዶችና የሴቶች ልጆች በድምሩ ስድስት የሩጫ ውድድሮች ይካሄዳል።

03:20 – 03:50 የአካል ጉዳተኛ ልጆች ሩጫ ውድድር አሸናፊዎች የሽልማት ስነ-ስርዓት ይካሄዳል።

03:50 – 04:05 የውድድሩን መልዕክት የተመለከተ ሽልማት የሚያስገኝ አጭር የጥያቄና መልስ ውድድር ይደረጋል።

04:05 – 04:25 የሽልማት ስነ-ስርዓት እና ሁሉም ውድድሩን ያጠናቀቁ ልጆች የዕጣ ሽልማት ስነ-ስርዓት ይካሄዳል።

ቦታ ፦ የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ (ኢምፔሪያል አጠገብ)

መኪና ማቆምያ፦

መኪና ከአካዳሚው ቅጥር ግቢ ውጪ ዋናውን በር ተከትሎ ወደ 22 መንገድ አቅጣጫ ማቆም የሚቻል ሲሆን ወላጆች ቀድመው እንዲደርሱ ይመከራል።

ጥበቃና ደህንነት፦

ራሳችሁን ከሌቦች ነቅታችሁ መጠበቅ አትዘንጉ፥ ተንቀሳቃሽ ስልክዎቻችሁን ካሜራና የመሳሰሉ ንብረቶቻችሁን በጥንቃቄ ያዙ። ልብ ይበሉ፤ የውድድሩን ቲሸርት ከለበሱ ልጆች ጋር ብቻ አዋቂዎች ወደ ቅጥር ግቢው የሚገቡ ይሆናል።

 

ፕሌይ ማተርስ

ፕሌይ ማተርስ ፕሮጀክት ትምህርትን በአዲስ እይታ በመቃኘት ከ 3-12+ ዓመት ያሉ ሕፃናትን ሁለንተናዊ እድገት እንዲሁም ቀጣይነት ያለው መማርን ማጎልበት ታሳቢ ያደረገ ሲሆን ይህንንም ለማሳካት ተማሪ ተኮር የማስተማር ሥነ-ዘዴን ይጠቀማል፡፡ አንድ ተግባር ተማሪ ተኮር የማስተማር ሥነ-ዘዴን መከተሉ በሚከተሉት አምስት ነጥቦች ማየት ይቻላል፡፡

  1. አስደሳችና አርኪ
  2. ለተማሪዎቹ ትርጉም ያለው ወይም ከተማሪዎቹ ጋር የሚዛመድ
  3. አሳታፊ በተግባርም በንግግር የሚሳተፉበት
  4. ሙከራን፤መላምት ማስቀመጥን የሚያበረታታ
  5. የእርስ በእርስ ተሳትፎ ያለበት ሲሆን ነው፡፡

ፕሌይ ማተርስ ፕሮጀክት ተማሪ ተኮር የማስተማር ስነ ዘዴን በመጠቀም የስደተኞች እና የተቀባይ ማህበረሰቡን ልጆች አጠቃላይ ትምህርትን፤ደህንነትን እና እድገትን ለማሻሻል ይፈልጋል፡፡ ተማሪ ተኮር የማስተማር ስነ-ዘዴ በኢትዩጵያ በቅድመ መደበኛ ት/ት እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች ላይ ተማሪን ማእከል ከሚያደርገው የትምህርት ስርአት ጋር አብሮ ይጣጣማል፡፡ በተጨማሪም መንግስት የመምህራኖችን ተማሪ ተኮር የማስተማር ስነ ዘዴን የመጠቀም አቅማቸውን ለማሻሻል በአገልግሎት ላይ  ላሉ መምህራን  የቅድመ አገልግሎት ስልጠና እና ቀጣይነት ያለው የሙያ ማጎልበቻ የስልጠና እድሎችን የማመቻቸት ስራ እየሰራ  ይገኛል፡፡

 ፕሌይ ማተርስ ፕሮጀክት ተማሪ ተኮር የማስተማር ስነ ዘዴን በመጠቀም የስደተኞች እና የተቀባይ ማህበረሰቡን ልጆች አጠቃላይ ትምህርትን፤ደህንነትን እና እድገትን ለማሻሻል ይፈልጋል፡፡ ተማሪ ተኮር የማስተማር ስነ-ዘዴ በኢትዩጵያ በ ኢሲዲ እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች ላይ ተማሪን ማእከል ከሚያደርገው የትምህርት ስርአት ጋር አብሮ ይጣጣማል፡፡ በተጨማሪም መንግስት የመምህራኖችን ተማሪ ተኮር የማስተማር ስነ ዘዴን የመጠቀም አቅማቸውን ለማሻሻል በአገልግሎት ላይ  መምህራን  የቅድመ አገልግሎት ስልጠና እና ቀጣይነት ያለው የሙያ ማጎልበቻ የስልጠና እድሎችን የማመቻቸት ስራ እየሰራ  ይገኛል፡፡

እነዚህን ጥረቶች ለመደገፍ፤ ፕሌይ ማተርስ ከት/ት ሚኒስቴር እና ከክልል የት/ት ቢሮዎች ጋር በጋራ ለመምህራን በተማሪ ተኮር የማስተማር ስነ-ዘዴ ላይ የሙያዊ እድገት እድል ለመስጥ እየሰራ ነው፡፡ ይኸውም  በስልጠና፤ ት/ትን ሲሰጡ የሚጠቀሙአቸውን የማስተማሪያ ሰነዶች በጋራ በመቅረፅ፤ ቀጣይነት ያለው ማስተማር እንዲሁም መምህራን ልምድ እንዲለዋወጡ እና እርስ በእርስ እንዲማማሩ የሚያስችሉ የአቻ ድጋፍ መድረኮችን በማዘጋጀት ነው፡፡

ይህ በተለይ ልጆችን ያማከለ ቴክኒኮችን በመጠቀም ትምህርቶችን በብቃት ለማድረስ የሚያስፈልጉ ዝቅተኛ የትምህርት ደረጃ፤ ስልጠና እና የማስተማር ስነ ዘዴ እውቀት ለሌላቸው በስደተኞች አካባቢ ላሉ መምህራን ጠቃሚ ነው፡፡ ክህሎታቸውን ለማሻሻል የሚሰጣቸው የሙያ ማጎልበቻ ስልጠና እድሎች ብዙ ግዜ ግዜአዊ እና በወረቅት ወደ ተረጋገጡ የት/ት ማስረጃዎች አያመሩም፡፡ የፕሌይ ማተርስ አካሄድ ስልታዊ እና ተቋማዊ እንዲሆን ለማድረግ ፕሮጀክቱ እየተተገበረ ባለበት ወረዳዎች ትግበራ ላይ ባለው በተከታታይ የመምህራን ሙያ ማሻሻያ ፕሮግራም ውስጥ በመምህራን ልማት መርሃግብር በመንግስት ተከታታይ ሙያዊ ልማት  ማእቀፍ ውስጥ ተማሪ ተኮር የማስተማር ስነ ዘዴ ማካተት የሚቻልበትን እድሎች ይቃኛል፡፡

ይህ ሁኔታ በእነዚህ አውዶች ውስጥ ያሉ መምህራን ከመምህራት ኮሌጆች ከፍተኛ መምህራን እና  አስተባባሪዎች ሙያዊ ድጋፍ እንዲያገኙ እና  ከፕሌይ ማተርስ ሙያተኞች የቴክኒክ ድጋፍ እንዲያገኙ እድል ይሰጣል፡፡ በዚህም ለእነዚህ መምህራን ዘላቂነት ያለው የማስተማሪያ ቴኒኮችን የሚያገኙ ሲሆን በሀገሪቱ ውስጥ የአገር ልማትን ለማምጣት ወሳኝ አካል የሆነውን የት/ት ጥራትን ለማሻሻል መንግስት የሚያደርገውን ጥረት ይደግፋል፡፡

ፕሌይ ማተርስ በኢትዮጵያ ውስጥ በጋምቤላ፣ በቤኒሻንጉል፣ በአፋር እና በሱማሌ ክልል በስደተኛ ካምፖች እና በማህበረሰቡ ውስጥ ላለፉት ሁለት አመታት ሲተገብር ቆይቷል፡፡

ውጤት ለማየት እዚህ ይጫኑ

ምዝገባው የሚደረገው በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ቢሮ ነው። 

ተጫማሪ መረጃዎች በሚኖሩ ጊዜ የምናሳውቅ ይሆናል።

ለበለጠ መረጃ

ስ.ቁ. 0116 635757

ኢሜይል፡info@ethiopianrun.org