የዱላ ቅብብል ውድድር
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ላለፉት 14 አመታት የዱላ ቅብብል ውድድር በአዲስ አበባ ሲያካሄድ ቆይቷል፡፡ ውድድሩ የመንገድ ደህንነትን በማስመልከት፣ ማለትም በቀለበት መንገድ አካባቢ የደረሱትን በርካታ አደጋዎች ምክንያት በማድረግ ተጀመረ፡፡ የመጀመሪያዎቹ ሦስት ውድድሮች በቀለበት መንገድ ላይ የተካሄዲ ሲሆን ከዚያ በኋላ የተከናወኑት ሁሉም ውድድሮች የአዲስ አበባ የመንገዶች ባለስልጣን እና ሲ.አር.ቢ.ሲ. አዲስ ኢንጂነሪንግ በሰሯቸው የተለያዩ አዳዲስ መንገዶች ላይ ተካሂደዋል፡፡
የሩጫው ርቀት፡ 8ኪሜ ሲሆን 8 ተወዳዳሪዎች በቡድን በመሆን አያንዳንዳቸው 1 ኪሜ ይሸፍናሉ
የሚፈቀደው የቡድን ብዛት፡ 150
ከአንድ ድርጅት የሚፈቀደው የቡድን ብዛት፡ 3
ውድድሩ በተለያዩ ምድቦች አወዳድሮ ይሸልማል፡፡ ቡድኖቹም እንደሚከተለው ናቸው፡
o የመጀመሪያው የኤምባሲ ቡድን
o የመጀመሪያው የንግድ ቡድን
o የመጀመሪያው የመንግስት መ/ቤት ቡድን
o የመጀመሪያው የስፖርት ማዘውተሪያ ቡድን
o የመጀመሪያው የሆቴሎች/የሬስቶራንቶች ቡድን
o የመጀመሪያው የመገናኛ ብዙሃን ቡድን
o የመጀመሪያው የልማት ወይም የእርዳታ ድርጅቶች ቡድን
o የመጀመሪያው የባኮች ቡድን
o የመጀመሪያው የጓደኛማቾች ቡድን
ከዚህ በተጨማሪም እስከ 50 የሚደርሱ የአትሌቲክስ ክለቦች በውድድሩ ላይ የሚሳተፉ ሲሆን እያንዳንዱ ክለብ 4 አትሌቶችን የሳትፋል፡፡ እያንዳንዱም አትሌት 3ኪ.ሜ. የሚሮጥ ይሆናል፡፡