2014 ሶፊ ማልት ሀዋሳ ግማሽ ማራቶን
Days
Hours
Minutes
Seconds
10ኛው ዙር ሶፊ ማልት ሐዋሳ ግማሽ ማራቶን ሩጫ ውድድር በውቧ ሐዋሳ ከተማ የካቲት 6 ቀን 2014ዓ.ም. ይካሄዳል። በዚህ ዓመት የ21ኪ.ሜ. ውድድር መነሻ አየር ማረፊያው አቅራቢያ የሐይቁን ዳርቻ ታኮ በተቀየሠ እዲስ የውድድር መስመር ይሆናል።
ውድድሩ የሚጠናቀቀው በመሐል ከተማ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ጋር ይሆናል።
ውድድሩ አራት ዐይነት ውድድሮችን ይይዛል
· 21ኪ.ሜ. የጤና ሯጮች የሚሳተፉበት
· የልጆች ሩጫ
· 21ኪ.ሜ. የአትሌቶች ሩጫ
· 7ኪ.ሜ. የጤና ሯጮች
በውድድሩ መስመር ላይ የሚጠጣ ውሃ ይሠጣል፤ እንዲሁም ተሣታፊዎችን ቀዝቀዝ ለማድረግ፣ ለማበረታታት እና ተዝናኖትን ለመጨመር የሻወር ጣቢያ ይኖራል።
ይህንን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ https://bit.ly/3DEt6Nt
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ፡ +251 116 635757 ወይም +251 116 633646 ኢሜይል፡ info@ethiopianrun.org
ለበለጠ መረጃ ፡ በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ቢሮ (ቦሌ መንገድ አለም ህንጻ 5ኛ ፎቅ) በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር +251 116 635 757 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ ፡፡
የምዝገባ አማራጮች – እባክዎን ቀደም ብለው ለሚመዘገቡ ቅናሽ የመግቢያ ክፍያዎች እንዳሉ ልብ ይበሉ! ሁሉም ዋጋዎች በኢትዮጵያ ብር ውስጥ ሲሆኑ 15% ተ.እ.ታ.