ታላቁ የቦቆጂ ሩጫ

Days
Hours
Minutes
Seconds

አገራችን ከምትታወቅባቸው መልካም ዕድሎች መካከል አትሌቲክስን መሠረት ያደረገው የስፖርት ቱሪዝም አንዱ ነው፡፡ ይህን መልካም ዕድል ወደተሟላ አገር አቀፍ ስኬታማነት ለመቀየር እንዲረዳ ቦቆጂን ማዕከል ያደረገ አገር አቀፍ ፕሮግራም ለማካሔድ ዝግጅት በመደረግ ላይ ነው፡፡

በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን የምትገኘው ቦቆጂ፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድር ከፍ ብላእንድትጠራ ያስደረጉ ስመጥር ዓለም አቀፍ አትሌቶች ፡- ኮማንደር ደራርቱ ቱሉን፣ ቀነኒሳ በቀለን እናጥሩነሽ ዲባባን ያፈራች ከተማ መሆኗ፤ አትሌትክስን ለማበረታታት እናከተማዋን የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የበለጠ ተመራጭ ያደርጋታል፡፡

የኢፌዲሪ ቱሪዝም ሚኒስቴር ከታላቁ ሩጫበኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ‘’ኢትዮጵያ ትሮጣለች’’ በሚል መሪ ቃልበቦቆጂ ከተማ ግንቦት 6 እና 7 ቀን
2014 ዓ.ም የአትሌቲክስ ስፖርት ውድድር ያካሂዳል፡፡ 

የዝግጅቱ ዋና ዓላማ የስፖርት ቱሪዝምን፣ በተለይም የአገር ውስጥ ቱሪዝምን ለማስፋፋት፣ የእውቅ ዓለም አቀፍ አትሌቶች መፍለቂያ የሆነችውን ቦቆጂ ከተማን ለማስተዋወቅ እና ከተማዋ እንድትነቃቃ በማድረግ ለአዳጊ አትሌቶች ጥሩ የመወዳደሪያ መድረክ ለመፍጠር ነው፡፡ 

ከአዲስ አበባ ለውድድሩ ለመሄድና ለመመዝገብ ለሚፈልጉ በታላቁ ሩጫ በኢትየጵያ ቢሮ፤ አለም ህንፃ 5ተኛፎቅ መመዝገብ ይችላሉ፡፡ የተራራ መውጣትና ሳይክል መንዳት ውድድር ሙሉመረጃ ማግኘት ከፈለጉ https://go.simienecotours.com/ridetherift

ከቦቆጂና አካባቢዋ ለመወዳደር ለሚገልጉ ተወዳዳሪዎች – በቦቆጂ ባጫ ህንፃ- ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ አጠገብ እናበከተማ አስተዳደር ቢሮ-
ሌሙና ቢልቢሉ ወረዳ አስተዳደር አጠገብ መመዝገብ ይችላሉ፡፡ 

ለበለጠ መረጃ ስልክ፡ +251 116 633 646; +251 116 635 757; +251 116 185841; +251 116 185 842  

ውጤት ለማየት እዚህ ይጫኑ

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሚከተላቸው የጎግሪን መርሆች

 1. ወረቀት መጠቀምን መቀነስ :
  ዛፎች በበዙ ቁጥር፣ ለኛም ጤናማ አየር እና መሮጫ ስፍራ ይበዛልናል! 

 2. የካርቦን ልቀትን መቀነስ
  ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ #ጎግሪን በሚለው መሰረት የካርቦን ልቀትን ለመቀነስ የራሱን አስተዋጽኦ ያደርጋል። ከነዚህ አንዱ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል 10 ኪ.ሜ ላይ የኤሌክትሪክ መኪና በመጠቀም ሩጫውን አስጀምሯል። 

 3. ቆሻሻን በየቦታው አለመጣል፡     
  በሁሉም ውድድሮች ላይ በየ 250ሜ. የቆሻሻ ማጠራቀሚያዎች በሩጫው ኮርስ ላይ ይቀመጣሉ. እሄም የፀዳ ውድድር እንዲኖረን ያደርጋል።

 4. ፕላስቲክ መጠቀምን መቀነስ ፡
  ፕላስቲክ መጠቀምን ለመቀነስ ለተሳታፊዎች ቀለል ያለ የፕላስቲክ ውሃ ጠርሙስ እንጠቀማለን. ለተሳታፊዎች ቦርሳ እንዲሁ ከፕላስቲክ ካልሆኑ ነገሮች የተሰራ ሲሆን ይህም እንደገና ጥቅም ላይ ማዋል ይችላሉ::

 5.  ቆሻሻ አሰባሰብን መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል:
  ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ፕላስቲኮችን መጠቀምን በመቀነስ ከባልደረባችን PETCO ጋር በ2021 ቶታልኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ  በኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል 10 ኪ.ሜ ላይ የደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብን መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል ተችሏል