ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሃ/የተ/የግል መገለጫ

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሃ/የተ/የግል መገለጫ

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሃ/የተ/የግል ማህበር የጎዳና ላይ ሩጫዎችን በማዘጋጀት የበርካታ አመታት ልምድ ያለው ድርጅት ነው፡፡ ከጅማሮው ጀምሮ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከ100 በላይ ሩጫዎችን በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍለ ሃገራት አከናውኗል፡፡ በዋና ከተማዋ ከሚካሄደው እና ታዋቂ ከሆነው አመታዊው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵየ በተጨማሪ በተለያዩ ክልል ከተሞች ሩጫዎችን ለማካሄድ ይሰራል፡፡ ታላቁ ሩጫ በነዚህ የስራ ጊዜዎቹ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ባለሞያዎችን ያካበተ ሲሆን፤ ከስፖንሰሮች ጋርም በመተባበር የተለያዩ የሚዲያ ሽፋኖች ላይ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በተለያዩ አፍሪካ ሃገራትም ውድድሮችን የማዘጋጀት ማማከር ስራም በመስራት ይታወቃል፡፡ ከነዚህም ውድድሮች ውስጥ የሚሊንየም ማራቶን በአክራ፤ ጋና እና ታላቁ የደቡብ ሱዳን ሩጫ በጁባ ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ራእይ፡- ሩጫን ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የአኗኗር ዘይቤ ማድረግ!
ተልዕኮ፡- ደረጃውን የጠበቀ፤ ብዙሃን ተሳታፊዎችን ያካተተ ሩጫ በማዘጋጀት የኢትዮጵያን ገፅታ መገንባት፤ ጤናማ አኗኗርን ማበረታታት፤ አስፈላጊ ማህበራዊ መልእክቶችን ማስተላላፍ እና ለታዳጊ አትሌቶች ጥሩ መድረክ መፍጠር፡፡