የአውሮፓ ቀን የህፃናት ውድድር
Days
Hours
Minutes
Seconds
የአውሮፓ ቀን የህፃናት ውድድር በየአመቱ የአውሮፓ አገሮች ህብረት ለመመስረት የተስማሙበትን ቀን ለማሰብ የሚደረግ የህፃናት ውድድር ነው፡፡ ውድድሩ በሁለቱም ፆታዎች እና በ4 የተለያዩ የእድሜ ክልልሎች (ማለትም ከ5 ዓመት በታች፣ ከ8 ዓመት በታች፣ ከ11 ዓመት በታች እንዲሁም ከ14 ዓመት በታች) የሚደረግ ሲሆን በየእድሜ ክልሉ አሸናፊ የሚሆኑት የሚሸለሙ ይሆናል፡፡
የምዝገባ ቀን እናሳውቃለን።
ለተጨማሪ መረጃ ለhenok@ethiopianrun.org ኢሜይል ይላኩ፡፡
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሚከተላቸው የጎግሪን መርሆች
- ወረቀት መጠቀምን መቀነስ :
ዛፎች በበዙ ቁጥር፣ ለኛም ጤናማ አየር እና መሮጫ ስፍራ ይበዛልናል! - የካርቦን ልቀትን መቀነስ ፡
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ #ጎግሪን በሚለው መሰረት የካርቦን ልቀትን ለመቀነስ የራሱን አስተዋጽኦ ያደርጋል። ከነዚህ አንዱ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል 10 ኪ.ሜ ላይ የኤሌክትሪክ መኪና በመጠቀም ሩጫውን አስጀምሯል። - ቆሻሻን በየቦታው አለመጣል፡
በሁሉም ውድድሮች ላይ በየ 250ሜ. የቆሻሻ ማጠራቀሚያዎች በሩጫው ኮርስ ላይ ይቀመጣሉ. እሄም የፀዳ ውድድር እንዲኖረን ያደርጋል። - ፕላስቲክ መጠቀምን መቀነስ ፡በዚህ አመት ለእንደገና ጥቅም ላይ ለማዋል ቀላል ለማድረግ ለተሳታፊዎች ቀለል ያለ የውሃ ጠርሙስ እንጠቀማለን. የእኛ ጥሩ ቦርሳ እንዲሁ ከፕላስቲክ ካልሆኑ ነገሮች የተሰራ ነው ይህም በተሳታፊዎች እንደገና ለመግዛት ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል::
- ቆሻሻ አሰባሰብን መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል:
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ፕላስቲኮችን መጠቀምን በመቀነስ ከባልደረባችን PETCO ጋር በ2021 ቶታልኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል 10 ኪ.ሜ ላይ የደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብን መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል ተችሏል