እንጦጦ ፓርክ ሩጫ
Days
Hours
Minutes
Seconds
የእንጦጦ ፓርክ ፕሬዲተር ሩጫ ውብ በሆነው የእንጦጦ የተፈጥሮ ፓርክ ውስጥ የሚካሄድ ወርሃዊ ውድድር ነው ፡፡
ሩጫው የሚከናወነው በግሪጎሪያን/ፈረንጆች አቆጣጠር የወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ ጠዋት 2:00 ሰዓት ላይ ነው ፡፡
በውድድሩ ለመሳተፍ እና ውጤትዎን ለማስመዝገብ ለውድድሩ በተዘጋጀው የመረጃ መረብ መመዝገብ አለበዎት፡፡ ውድድሩ ከክፍያ ነፃ ሲሆን በየወሩ በ 700 ቦታዎች ብቻ የተወሰነ ነው ፡፡ ምዝገባው ቅድሚያ ለተመዘገበ ቅድሚያ አገልግሎት በሚለው መርህ ይመራል ፡፡
ምዝገባው በግሪጎሪያን አቆጣጠር የወሩ የመጨረሻ ሰኞ ጠዋት 12፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል ፡፡
ለበለጠ መረጃ +251 663 57 57
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሚከተላቸው የጎግሪን መርሆች
- ወረቀት መጠቀምን መቀነስ :
ዛፎች በበዙ ቁጥር፣ ለኛም ጤናማ አየር እና መሮጫ ስፍራ ይበዛልናል! - የካርቦን ልቀትን መቀነስ ፡
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ #ጎግሪን በሚለው መሰረት የካርቦን ልቀትን ለመቀነስ የራሱን አስተዋጽኦ ያደርጋል። ከነዚህ አንዱ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል 10 ኪ.ሜ ላይ የኤሌክትሪክ መኪና በመጠቀም ሩጫውን አስጀምሯል። - ቆሻሻን በየቦታው አለመጣል፡
በሁሉም ውድድሮች ላይ በየ 250ሜ. የቆሻሻ ማጠራቀሚያዎች በሩጫው ኮርስ ላይ ይቀመጣሉ. እሄም የፀዳ ውድድር እንዲኖረን ያደርጋል። - ፕላስቲክ መጠቀምን መቀነስ ፡በዚህ አመት ለእንደገና ጥቅም ላይ ለማዋል ቀላል ለማድረግ ለተሳታፊዎች ቀለል ያለ የውሃ ጠርሙስ እንጠቀማለን. የእኛ ጥሩ ቦርሳ እንዲሁ ከፕላስቲክ ካልሆኑ ነገሮች የተሰራ ነው ይህም በተሳታፊዎች እንደገና ለመግዛት ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል::
- ቆሻሻ አሰባሰብን መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል:
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ፕላስቲኮችን መጠቀምን በመቀነስ ከባልደረባችን PETCO ጋር በ2021 ቶታልኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል 10 ኪ.ሜ ላይ የደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብን መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል ተችሏል