የ2015 ሶፊ ማልት ሀዋሳ ግማሽ ማራቶን ላይ ለሚሳተፉ አትሌቶች ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት ተዘጋጅቷል

ጥር 3 ቀን 2015 ዓ.ም.፡- እሁድ የካቲት 05 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚካሄደው የ2015 ሶፊ ማልት ሀዋሳ ግማሽ ማራቶን አትሌቶች ውድድር አጠቃላይ ከ400,000 ብር በላይ ሽልማት እንደሚሆን የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አዘጋጆች አሳወቁ። ሽልማቱ ውድድሩን (ግማሽ ማራቶኑን) ከ60 ደቂቃ በታች ለሚጨርሱ ማንኛውም ወንድ አትሌቶች እና ከ70 ደቂቃ በታች ለሚጨርሱ ሴት አትሌቶች በየዘርፋቸው የሚከፋፈሉት የ100,000 ብር ሽልማትን ያካትታል። […]

የ2015 ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ ዘመቻ የታቀደለትን ገቢ አሰባስቦ ለሶስት በጎ አድራጎት ድርጅቶች አስረከበ፡፡

በዘመቻው ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በተለያዩ መንገዶች ተሰብስቧል፡፡ ታህሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም.፡- ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ቢሮ ጋር በመተባበር የተለያዩ ማህበራትን ሲደግፍ የቆየው ሌሎችን ለመርዳት ሮጣለሁ ዘመቻ ዘንድሮም ሶስት የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን ታሳቢ ያደረገ የገቢ ማሰባሰቢያ ሲያደርግ እንደነበር ይታወቃል፡፡ የ2015 ሶፊ ማልት ቃላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. አካል የሆነው […]

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ “ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ” በሚል ፕሮግራሙ ያሰባሰበውን የ1.8 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለአራት በጎ አድራጊ ድርጅቶች አበረከተ::

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ “ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ” በሚል ፕሮግራሙ ያሰባሰበውን የ1.8 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለአራት በጎ አድራጊ ድርጅቶች አበረከተ:: ኃይለእግዚአብሔር አድሐኖም – ታህሳስ 11/2011 ዓ.ም ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከዚህ በፊት በነበሩት አመታት እንደሚያደርገው ሁሉ፡ ከሚያከናውነው አመታዊ የታላቁ ሩጫ የ10ኪ.ሜ የጎዳና ላይ የአትሌቲክስ ውድድር ጎን ለጎን የበጎ አድራጎት ስራ የሚያከናውኑ ድርጅቶችን በገንዘብ ለማገዝ፡ ‘ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ’ በሚል […]

‘ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ’ – ጋዜጣዊ  መግለጫ

ሩጫን በምክንያት መሮጥ- ‘ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ’ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ፕሮግራም ሃሙስ ታህሣሥ 11 – ለ18ተኛ ጊዜ ከተካሄደው ቶታል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር ተያይዞ ለ6ተኛ ጊዜ የተካሄደው ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ ፕሮግራም በዚህኛውም አመት በተወሰኑ የታላቁ ሩጫ ተሳታፊዎች እና ድርጅቶች በጎ ፈቃደኝነት ከታቀደለት 1.7 ሚሊዮን ብር አስበልጦ 1.8 ሚሊዮን ብር ለማሰባሰብ ችሏል፡፡ እንደወትሮው 4 የተለያዩ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን […]