አካቶ ስፖርት – በታላቁ ሩጫ

“ስፖርት እወዳለሁ፡፡ በተለይ ለእግር ኳስ ያለኝ ፍቅር ይህ ነው አይባልም፡፡ “ገና ትንሽ ልጅ ሆኜ እንኳን አብረውኝ የሚማሩ ልጆች ኳስ ይዘው ወደ ሜዳ ሲሄዱ እከተላቸዋለሁ፡፡ ልጫወት፡፡ ነገር ግን ተጫውቼ አላውቅም፡፡ ገና ቡድን ሲመራረጡ አንተ ልብስና ደብተር ጠብቅ እባላለሁ፡፡ ሌላም ጊዜ ተስፋ ሳልቆርጥ አብሬያቸው እሄዳለሁ፡፡ እነርሱ ግን ሁልጊዜ ጠባቂ ያደርጉኛል፡፡ እንደማይጠሉኝ አውቃለሁ፡፡ ብዙ ቦታ ለእኔ የማይመች አጋጣሚ […]

“ታላቁ ሩጫ – ለተስፈኞች ተስፋ” ይግረም ደመላሽ

ይግረም ደመላሽ – የሪዮ ኦሊምፒክ ዲፕሎማ ተሸላሚና የመጪው ዓለም ሻምፒዮና ተስፈኛ ተወልዶ ያደገው በምዕራብ ጎጃም ደጋ ዳሞት ወረዳ ልዩ ስሙ ድኩል ቃና በሚባል ስፍራ ሲሆን በግብርና ስራ የሚተዳደሩት ወላጆቹ ካፈሯቸው ሁለት ወንድ እና ሁለት ሴት ልጆች ሶስተኛው ነው፡፡ በልጅነቱ በእረኝነት ስራ ቤተሰቦቹን ከማገዙ ጎን ለጎን የገና ጨዋታን ጨምሮ ሩጫ የተቀላቀለባቸው የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ያዘወትር ነበር፡፡ የሩጫ […]

ታላቁ ሩጫ ላይ ያላሸነፍኩባቸው አምስት ሰበቦች (ሎል

ታላቁ ሩጫ እንደ እንቁጣጣሽ የሕዝብ በዓል መሆኑ ሁሌም ሲደርስ ብቻ ነው የሚገባኝ፡፡ የዘንድሮው ትኬት በአንድ ሳምንት ተሸጦ በማለቁ፣ ከአትራፊዎች ለመግዛት ያላየነው ፍዳ አልነበረም – ደግነቱ ተሳክቷል፡፡ ነገር ግን ‹‹እንደተጠበቅኩት›› አንደኛ ሳልወጣ ቀርቼያለሁ፡፡ ሰበብ አለኝ፡፡ ምናልባት እናንተ ግምታችሁን ስትሰነዝሩ ‹‹ጫማው ስለጠበበው፣ በዋዜማው የበላው እራት ስላልተስማማው፣ ውድድሩ በተጀመረ ሰባተኛው ደቂቃ ላይ ሆድ ቁርጠት ስለጀመረው፣ የዳኞች አድሎ ስለነበር….›› […]