የዝግታ ግማሽ ማራቶን ሯጩ ማስታወሻ ~ዳግም ተሾመ
የሃዋሳ ግማሽ ማራቶን ውድድር ሲጀመር ጀምሮ በአዘጋጅ ቡድን አባልነት ተሳትፌአለሁ፡፡ በተለያዩ አመታት የውድድሩ መንገድ ሲለካ አንዴም ባለ 3 ዙር አንዴም ባለ 2 ዙር ስለሚሆን ሙሉውን ግማሽ ማራቶን ሮጬው አላውቅም፡፡ ባለፈው አመት ግን የውድድሩ መንገድ አንድ ወጥ 21ኪ.ሜ. በመሆኑ መንገዱን ለመለካት ሙሉውን በሳይክል የመጓዝ እድሉ ነበረኝ፡፡ ነገር ግን ሳይክል መንዳት እና መሮጥ ለየቅል ናቸው፡፡ ውድድሩን ካካሄድን […]
ስፖርት እና ማህበረሰብ
ቀለል ያለው አለባበሱ በስፖርት የዳበረ ሰውነቱን ባይደብቅበትም ስፖርተኞቹን መቀላቀል አልፈለገም፡፡ የ39 ዓመቱ ውብሸት መንግስቱ ጥግ ይዞ አድፍጧል፡፡ የሀዋሳ ግማሽ ማራቶን በተካሄደበት ባለፈው የሚያዚያ አጋማሽ እሁድ ጠዋት አስቀድመው “ገብርኤል አደባባይ” አቅራቢያ የተሰባሰቡትን ሯጮች በተመስጦ ይመለከታል፡፡ “ታውቃለህ… ከሯጮቹ የማውቀው ሰው አላየሁም” ይላል በመገረም የአንድ እጁን መዳፍ አፉ ላይ ጭኖ፡፡ የእድሜውን ሶስት አራተኛ በሀዋሳ የኖረው ውብሸት እንደ ቀደመው […]
ጂሮ ሞሺዙኪ
በትንንሽ አይኖቹ ታላላቆችን አይቶ ያሳየን ፎቶግራፈር ጂሮ ሞሺዙኪ ይባላል፡፡ በቶኪዮ ተወልዶ መኖሪያውን በፓሪስ ያደረገ ጃፓናዊ ፎቶግራፈር ነው፡፡ በአለም ዙሪያ እየተጓዘ የአትሌቲክስ፣ እግር ኳስ እና ራግቢ ታላላቅ ውድድሮችን በካሜራው መያዝ ከጀመረ ከ30 ዓመታት በላይ ቆጥሯል፡፡ የስፖርታዊ ትዕይንቶች እና ሌሎችም ስራዎቹን በትልልቅ ሙዚየሞች እና ጋለሪዎች ለህዝብ የሚያሳየው ጂሮ ከኢትዮጵያውያን ታላላቅ አትሌቶች ጋር ልዩ የሚባል ቁርኝት አለው፡፡ ከጥቂት […]
የጃኖዎቹ – ሔዋንና ሃሌሉያ
ሔዋን ትሮጣለች፡፡ ድምጻዊት እንደመሆንዋ በተለይ የመንገድ ሩጫን እንደ ጥሩ ትንፋሽ ማስተካከያ ትጠቀምበታለች፡፡ ሙዚቃ እየሰማች እስከ 6ኪሎ ሜትር ትሮጣለች፡፡ አካላዊ ብርታትዋን እና ጥንካሬዋን ለመጠበቅ ደግሞ ወደ ጂም ትሄዳለች፡፡ “በይበልጥ ግን መንገድ ላይ የምሮጠው ይበልጣል” ትላለች፡፡ ጃኖ ከመጀመሯ ቀደም ባለው ጊዜ እንዲያውም ክብደቷን ለመቆጣጠር እና በሌሎችም ምክንያቶች በሳምንት ሰባቱን ቀናት የምትሰራበት ጊዜ ነበር፡፡ “ስቴጅ ላይ ትንፋሽ ያስፈልጋል፡፡ […]
ኢትዮጵያ እና ሩጫ
የ19 አመቷ ዮዲት ፓልመር (ስሟ የተቀየረ) በአሜሪካ ሀገር ትኖራለች፡፡ ገና በአራት አመቷ በጉዲፈቻ ከሀገሯ የወጣችው ወጣት አማርኛ ቋንቋ አትናገርም፡፡ አትሰማምም፡፡ ሆኖም በኢንተርኔት ስለ ኢትዮጵያ ለማወቅ ትሞክራለች፡፡ በአጋጣሚዎች ሁሉ ስለ ኢትዮጵያ እያነሳች አሜሪካዊያን ጓደኞቿ ስለ ሀገሯ የሚያውቁትን ለመስማት ትፈልጋለች፡፡ ካወራቻቸው በቁጥር የበዙት “ኢትዮጵያውያን ሯጮች ናቸው” ይሏታል፡፡ የሀይሌ ገ/ስላሴን እና ሌሎችንም ታላላቅ አትሌቶች ስም እያስታወሱ ይነግሯታል፡፡ “በዜግነቴ […]
የፎቶ አንሺዎቹ ሩጫ
በ17ኛው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የ10 ኪ.ሜ. ውድድር ላይ ከ40 ሺህ በላይ የሆኑ ሰዎች ተሳትፈዋል። ሁሉም የሚሳተፉበት የየራሳቸው ምክኒያት ቢኖራቸውም አብዛኞቹ የተቀራረበ አላማ ይዘው ይሮጣሉ ፣ ዱብዱብ ይላሉ፣ ይራመዳሉ። ምክንያታቸው ደግሞ ፤ ባለፉት አመታት የገቡበትን ሰዓት ለማሻሻል ከመሮጥ አንስቶ 10ኪ.ሜ. ለመጨረስ እስከመፈለግ ፣ ከቅርብ ጓደኞች እና ቤተሰቦቻቸው ጋር በስፖርት ለመዝናናት ከመሻት አንስቶ ከድሮ ወዳጆቻቸው ጋር ተገናኝቶ […]
አሠፋ መዝገቡ – አትሌቱ!
ይህ ስም በኢትዮጵያ ታዋቂ ነው – አሠፋ መዝገቡ፡፡ ከ25 ዓመት በታች የሆኑትን ወጣቶች “አሠፋ መዝገቡ” ማነው? ብላችሁ ጠይቋቸው፡፡ ሳያመነቱ “ትራፊክ ነዋ!” ይሏችኋል፡፡ ከፍ ያሉትን ጠይቋቸው፡፡ “አሠፋ መዝገቡ” ማነው? እነዚህኞቹ ምናልባትም ጥያቄያችሁን በጥያቄ ይመልሱላችኋል፡፡ “አሠፋ መዝገቡ አትሌቱ? ወይስ ትራፊኩ?” አሁን ዱብ ዱብ እንግዳ አድርጋ የምታቀርብላችሁ የኦሊምፒክ ሜዳሊያ ባለቤቱ እና የሌሎች በርካታ ሜዳሊያዎች አሸናፊው አትሌቱ አሠፋ መዝገቡ […]
አንዱዓምላክ በልሁ
“ለታላቁ ሩጫ እየተዘጋጀሁ ነው” ልጁ ስመ ብዙ ነው፡፡ ወንድሞቹ “ሀብታሙ” ይሉታል፡፡ እናት እና አባቱ በጉራጊኛ “ካብቱ” (ሀብታሙ) ብለው ይጠሩታል፡፡ አያቱ ደግሞ ከህጻንነቱ አንስቶ “ስራህ ብዙ” ይሉታል፡፡ “ተናጋሪ እና ቀልቃላ ቢጤ ስለነበርኩ መሰለኝ” ይላል የስሙ ባለቤት፡፡ የ21 አመቱ ወጣት ባለፉት አራት ዓመታት ብዙ ተለውጧል፡፡ በ2005 ዓ.ም. የስምንተኛ ክፍል ፈተናውን ከወሰደ በኋላ ሁሉም ነገር በፍጥነት እንደሆነ ይናገራል፡፡ […]
ሰንበሬ ተፈሪ ሶራ – ኢትዮጵያ (1500ሜ.፣ 3000ሜ.፣ 5000ሜ.፣ 10,000ሜ.፣ አገር አቋራጭ)
የትውልድ ዘመን፡- ሚያዝያ 25/1987 የትውልድ ስፍራ፡- ኦሮሚያ ክልል ጉጂ ቁመት፡- 1.62 ሜ. ክብደት፡- 45 ኪ.ግ. ማናጀር፡- ሁሴን ማኪ ክለብ፡- ፌደራል ማረሚያ ቤቶች ሰንበሬ ተፈሪ ወደሩጫው ዓለም የተቀላቀለችው በደቡብ ኢትዮጵያ ጉጂ ዞን በ2002 ዓ.ም. የአትሌት መልማዮች የምትማርበት ትምህር ቤት ድረስ መጥተው ምርጫ ባደረጉበት አጋጣሚ ነበር፡፡ ስድስት ወንድም እና ሶስት እህቶች ያሏት ሰንበሬ በግብርና ስራ የሚተዳደሩት ወላጆቿ […]
አርቲስት አለማየሁ ታደሰ፡- ‘ታላቁ ሩጫ የማይቻል መስሎን ነበር’
ዱብዱብ፡- አርቲስት አለማየሁ ጥሩ የሚባል ቁመና ላይ ትገኛለህ፡፡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ታደርጋለህ? አለማየሁ፡- አዎ፡፡ ሌላው ቀርቶ ወደ መድረክ ከመውጣታችን በፊት የተለያዩ ስፖርቶችን እንሰራለን፡፡ ሁለት ሰዓታት ያህል ጊዜ የሚወስዱ ቴአትሮችን በብቃት ለመወጣት የአካል ብቃት ይጠይቃል፡፡ ቀደም ሲል ጂምናዚየም ውስጥ ስፖርት እሰራ ነበር፡፡ በኋላ ግን የወገብ ህመም ገጠመኝና ዎክ /እርምጃ/ እና ሶምሶማ አደርጋለሁ፡፡ ከሁሉ በፊት ግን ዮጋ […]