የ2015 ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ ዘመቻ የታቀደለትን ገቢ አሰባስቦ ለሶስት በጎ አድራጎት ድርጅቶች አስረከበ፡፡

በዘመቻው ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በተለያዩ መንገዶች ተሰብስቧል፡፡ ታህሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም.፡- ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ቢሮ ጋር በመተባበር የተለያዩ ማህበራትን ሲደግፍ የቆየው ሌሎችን ለመርዳት ሮጣለሁ ዘመቻ ዘንድሮም ሶስት የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን ታሳቢ ያደረገ የገቢ ማሰባሰቢያ ሲያደርግ እንደነበር ይታወቃል፡፡ የ2015 ሶፊ ማልት ቃላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. አካል የሆነው […]

የ2015 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ውድድር አካል የሆነው ሌሎችን ለመርዳት ሮጣለሁ የእርዳታ ማሰባሰብ ዘመቻ ያቀደውን 1 ሚልዮን ብር አሰባሰበ፡፡

ህዳር 5 ቀን 2015 ዓ.ም.፡- ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በመተባበር ሌሎችን ለመርዳት ሮጣለሁ አመታዊው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻ ዘንድሮ 1 ሚሊዮን ብር ለማሰባሰብ አቅዶ እየሰራ እንደነበር ይታወቃል፡፡ በየአመቱ እንደሚያደርገውም የተመረጡትን አክሽን ፎር ዴቨሎመንት (በድርቅ የተፈናቀሉ ወገኖች ላይ የሚሰራ)፤ ኢማጅን ዋን ደይ (ህፃናት ላይ የሚሰራ) እና ምዥዥጓ ሎካ የሴቶች ማጎልበቻ ማህበር ተጠቃሚዎች ያደርጋል፡፡ […]

ፔሬስ ጄፕቺርችር – የ2015 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ የክብር እንግዳ መሆኗ ታወቀ፡፡

ጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ.ም.፡- እ.ኤ.አየ2020 ቶኪዮ ኦሎምፒክ አሸናፊዋ ፔሬስጄፕቺርችር እሁድ ህዳር 11 ቀን በሚደረገው የ2015 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ ውድድር ላይ የክብር እንግዳ እንደምትሆን ታውቋል፡፡ የ29 አመቷ ፔሬስ በ2021 ባልተለመደ መልኩ የኒውዮርክ ማራቶንን እና የኦሎምፒክ አሸናፊነትን ያገኘች ሲሆን በ2022 ደግሞ በግሩም ብቃት የቦስተን ማራቶንን አሸንፋለች፡፡ ፔሬስ የ2016 እና የ2020 የሁለት […]

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሚዲያ አጋርነት ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሚዲያ አጋርነት ስምምነት ተፈራረሙ፡፡  “ባለፉት ሃያ ዓመታት ታላቁ ሩጫ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ማሰባሰብ ችሏል፧ በዓመት አንዴ ስለ ሰላም፣ ስለ ፍቅር፣ ስለ አብሮነት ልባቸውን እንዲሰጡ አድርጓል: በሐይማኖታዊ በዓላት አብረው መሆን ያልቻሉ ዜጎች በታላቁ ሩጫ ተቃቅፈው ይሮጣሉ፤ በብሔረሰባዊ መሰባሰቦች አንድ ላይ መሆን ያልቻሉ ሕዝቦች ታላቁ ሩጫን ጠብቀው […]

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የ 22ኛ ዙር ውድድር 40ሺ የመሮጫ ቦታዎች ውስጥ ግማሹን አገባደደ፡፡

ከተለያዩ ሃገራት የሚመጡ ተሳታፊዎችን ለማስተናገድ እየተዘጋጀ ያለው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የ 22ኛ ዙር ውድድር 40ሺ የመሮጫ ቦታዎች ውስጥ ግማሹን አገባደደ፡፡ የ2015 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለምአቀፍ 10ኪ.ሜ. ለ22ኛ ጊዜ ሊካሄድ ዝግጅት ተጀምሯል፡፡ትምህርት ለሁሉም ህፃናት የዘንድሮ የሩጫ መልዕክት ነው፡፡ዘንድሮ 40ሺ ተሳታፊዎች የሚሳተፉ ሲሆን ይህ ቁጥር ባለፉት 2 አመታት በነበረው ወረርሽኝ ምክንያት ቀንሶ የነበረውን ተሳታፊ ቁጥር […]

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. በ”RUNNERS WORLD” ምርጥ 10ኪሜ ሩጫዎች ዝርዝር ውስጥ ተቀዳሚውን ቦታ አግኝቷል፡፡

ግንቦት 09 ቀን 2014 ዓ.ም. – ለ21 አመታት ያለመቋረጥ የተካሄደው እና ለበርካታ አትሌቶች የመፎካከሪያ መድረክ በመፍጠር ተቀዳሚ ቦታን የያዘው አመታዊው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል 10ኪሜ ውድድር በየወሩ የሚወጣው ራነርስ ወርልድ መፅሄት በዚህ ወር ዝርዝሩ ላይ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በአለም ላይ ካሉ ታዋቂ የ10ኪሜ ውድድሮች ውስጥ በቀዳሚነት ተጠቃሽ ነው ሲል አስፍሮታል፡፡ ራነርስ ወርልድ የተለያዩ የሩጫ ዜናዎችን፤ […]

የ2014 ቶታልኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አትሌቶች ውድድር በኢሌክትሪክ መኪና ይመራል፡፡

ጥር 9 ቀን 2014 ዓ.ም፡- ጥር 15 ቀን የሚካሄደው የ2014 ቶታልኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የወንድ እና ሴት አትሌቶች ውድድር በኢትየጵያ የኤሌክትሪክ መኪና በማስመጣት በሚታወቀው ግሪን ቴክ አማካኝነት በተዘጋጁ የኤሌክትሪክ መኪኖች የሚመራ እንደሆነ ታውቋል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በኤሌክትሪክ መኪና የሚደረገው የአትሌቶች እጀባ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በዘንድሮው አመት ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተዋወቀውን እና በ2014/15 የሚደረጉ ሁሉም ውድድሮች ላይ ግንዛቤ […]

ዶ/ር ሴቶር ኖርግቤ በ2014 ቶታልኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል 10ኪ.ሜ. ላይ ተሳታፊ ትሆናለች፡፡

ዶ/ር ሴቶር ኖርግቤ በ2014 ቶታልኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል 10ኪ.ሜ. ላይ ተሳታፊ ትሆናለች፡፡ ታህሳስ 06 2014 ዓ.ም. ፡- የጋና የ2021 የቁንጅና ውድድር በጣም ቆንጆ አሸናፊ እና ስለ አፍሪካ አንድነት ጠንካራ አቀንቃኝ ዶ/ር ሴቶር ኖርግቤ እሁድ ጥር 15 ቀን በ2014 ቶታልኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ላይ ተሳታፊ እንደምትሆን ታውቋል፡፡ ሩጫው ላይ ከመሳተፍም በተጨማሪ አርብ ጥር 13 ቀን […]

300 ሰዎች በላይ በተለያዩ የአለማችን ክፍል የሚኖሩ ተሳታፊዎች የ2014 ቶታልኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. ውድድር ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 5 ቀን አካሂደዋል፡፡

የ2014 ቶታልኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. ውድድር ላልተወሰነ ጊዜ ቢራዘምም ከ300 ሰዎች በላይ በተለያዩ የአለማችን ክፍል የሚኖሩ ተሳታፊዎች በያሉበት ሆነው የግል ሩጫቸውን ባሳለፍነው ሳምንት ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 5 ቀን አካሂደዋል፡፡ በዚህ ውድድር ላይ 10 የሚሆኑ ሃገራትን የወከሉ ተወዳዳሪዎች ተሳታፊዎች ሆነዋል፤ ተሳፊዎች ያሳለፉትን ሩጫ በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ማህበራዊ ገፆች ላይ @GreathEthRun (ትዊተር) ወይም / @GreatEthiopianRun […]

የ2014 ቶታልኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል 10ኪ.ሜ የክብር እንግዳ አትሌት ፌዝ ኪፕዮገን መሆንዋ ታወቀ፡፡

ጥቅምት 15 ቀን 2014 ኬንያዊቷ እና የሁለት ጊዜ ኦሎምፒክ አሸናፊዋ ፌዝ ኪፕዮገን የ2014 ቶታልኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የክብር እንግዳ እንደምትሆን ታወቀ፡፡ በ1500 ሜትር ውድድር በሪዎ እና ቶኪዮ ኦሎምፒክ አሸናፊ የሆነችው ኪፕዮገን ህዳር 05 ቀን በሚካሄደው ውድድር ላይ በክብር እንግድነት የምትገኝ ይሆናል፡፡ ባሳለፍነው አመት ማገባደጃ ላይ በተካሄደው የቶኪዮ ኦሎምቲክ ውድድር ላይ በማሸነፏ በ1500 ሜትር የአለም ቀዳሚ […]