አዲስ አበባን የስፖርት ቱሪዝም መዳረሻ በማደረግ የሚገባትን ገፅታ ለማምጣት በስፖርትና መዝናኛ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ለመሥራት የሚያስችል ስምምነት ተካሄደ ።

ሰኔ 1፣ 2014 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ፣ በወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ እና በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መካከል በዛሬው እለት በከተማዋ እንደ ስፖርት ያሉ ቱሪስቶች የመሳብ አቅም ያላቸውን እንቅስቃሴዎች በጋራ በመተባበር፣ በማልማትና በማበልፅግ የስፖርት ቱሪዝምን እንዲስፋፋ ለመስራት የሶስትዮሽ ስምምነት ተፈራርመዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ ክብርት ዶክተር ሂሩት ካሳው፣ […]

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. በ”RUNNERS WORLD” ምርጥ 10ኪሜ ሩጫዎች ዝርዝር ውስጥ ተቀዳሚውን ቦታ አግኝቷል፡፡

ግንቦት 09 ቀን 2014 ዓ.ም. – ለ21 አመታት ያለመቋረጥ የተካሄደው እና ለበርካታ አትሌቶች የመፎካከሪያ መድረክ በመፍጠር ተቀዳሚ ቦታን የያዘው አመታዊው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል 10ኪሜ ውድድር በየወሩ የሚወጣው ራነርስ ወርልድ መፅሄት በዚህ ወር ዝርዝሩ ላይ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በአለም ላይ ካሉ ታዋቂ የ10ኪሜ ውድድሮች ውስጥ በቀዳሚነት ተጠቃሽ ነው ሲል አስፍሮታል፡፡ ራነርስ ወርልድ የተለያዩ የሩጫ ዜናዎችን፤ የስልጠና ጠቃሚ መልእልቶችን፤ […]

የአይኤፍኤች ኢንጂነሪንግ 20ኛ አመት የምስረታ በአል ከሳርቤት እስከ ጎተራ በዱላ ቅብብል ውድድር ሊያከብር ነው

አይኤፍኤች ኢንጂነሪንግ (በቀድሞ ስሙ ‘ሲአርቢሲ አዲስ ኢንጂነሪንግ’ ተብሎ ይንቀሳቀስ የነበረው) እሁድ ሐምሌ 10 ቀን 2014 የሚካሄደውን የ2014 የአይኤፍኤች የዱላ ቅብብል ስፖንሰር በማድረግበኢትዮጵያ የ20 ዓመታት ስራውን ያከብራል። ውድድሩ የሚካሄደው በአይኤፍኤች በተጠናቀቀው ከሳርቤት ፑሽኪን አደባባይ ወደጎተራ ማሳለጫ መንገድ ከአዲስ አበባ በደቡብ በኩል ባለው አዲስ መንገድ ላይ ነው። አይኤፍኤች ኢንጂነሪንግ እነዚህን የዱላ ቅብብሎሽ ለመጀመሪያ ጊዜ ስፖንሰር ያደረገው በ 1997 ዓ.ም ከቃሊታ እስከ መገናኛ ባለው የአዲስ አበባ ቀለበት መንገድ ምስራቃዊ ዝርጋታ መጠናቀቁን ምክንያት በማድረግ ነበር። በ1999 ለሦስተኛ ጊዜ በድጋሚ ከተካሄደው የዱላ ቅብብል ውድድር በኋላ ኩባንያው ከአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን (አአአክራ) ጋር በመተባበር ዝግጅቱን በከተማዋ ወደሚገኙ ሌሎች ቦታዎች ተዘዋውሮ ባስገነባቸው ሌሎች አዳዲስ መንገዶች ላይ አክብርዋል። በቅርብ ጊዜ የተካሄደው፣ 16 ኛው ተከታታይ አመታዊ የዱላ ቅብብል ውድድር፣ የተካሄደው ከሦስት ዓመታት በፊት በ 2011 የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከመከሰቱ በፊት ነበር። ባለፉት ሃያ ዓመታት አይኤፍኤች ኢንጂነሪንግ የመንገድና ድልድይ ግንባታ ፕሮጀክቶቹን ባከናወነበት ፍጥነት መልካም ስም አትርፏል። ከፕሮጀክቶቹ መካከል የአዲስ አበባ ቀለበት መንገድ፣ የኢትዮ-ቻይና ወዳጅነት መንገድ በወሎ ሰፈር፣ የቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ማኮብኮቢያ ማሻሻያና ማስፋፊያ ፕሮጀክት፣ ከመገናኛ እስከ አያት መንገድ፣ ከመገናኛ እስከ ጦርኃይሎች መንገድ፣ ከመስቀል አደባባይ እስከ ቃሊቲ መንገድ ድረስ ያሉ ፕሮጀክቶች ይገኙበታል። […]

ሶፊ ማልት በአፍሪካ ትልቁ የሆነውን የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ስያሜ ወሰደ

ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም. የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አዘጋጆች ህዳር 11 ቀን 2015 ዓ.ም. ለ22ኛ ጊዜ ለሚያካሂዱት ውድድር የስያሜ ስፖንሰር ሶፊ ማልት መሆኑን አሳውቀዋል፡፡ ሄኒከን ኢትዮጵያ በሶፊ ማልት ምርቱ ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር ከዚህም በተጨማሪ የተለያዩ ውድድሮች ላይ በአጋርነት ይሰራል፡፡ ሳምራዊት ግርማ የሄኒከን ስፖንሰርሽፕ እና ብራንድ ማናጀር የዚህ ስምምነት መጠናቀቅን አስመልክተው “በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሚዘጋጁ […]

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. በ”RUNNERS WORLD” ምርጥ 10ኪሜ ሩጫዎች ዝርዝር ውስጥ ተቀዳሚውን ቦታ አግኝቷል፡፡

ግንቦት 09 ቀን 2014 ዓ.ም. – ለ21 አመታት ያለመቋረጥ የተካሄደው እና ለበርካታ አትሌቶች የመፎካከሪያ መድረክ በመፍጠር ተቀዳሚ ቦታን የያዘው አመታዊው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል 10ኪሜ ውድድር በየወሩ የሚወጣው ራነርስ ወርልድ መፅሄት በዚህ ወር ዝርዝሩ ላይ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በአለም ላይ ካሉ ታዋቂ የ10ኪሜ ውድድሮች ውስጥ በቀዳሚነት ተጠቃሽ ነው ሲል አስፍሮታል፡፡ ራነርስ ወርልድ የተለያዩ የሩጫ ዜናዎችን፤ […]

ቱሪዝም ሚኒስቴር ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ

ሚያዚያ 7 ቀን 2014፡- አገራችን ከምትታወቅባቸው መልካም ዕድሎች መካከል አትሌቲክስን መሠረት ያደረገው የስፖርት ቱሪዝም አንዱ ነው፡፡ ይህን መልካም ዕድል ወደ ተሟላ አገር አቀፍ ስኬታማነት ለመቀየር እንዲረዳ ቦቆጂን ማዕከል ያደረገ አገር አቀፍ ፕሮግራም ለማካሔድ ዝግጅት በመደረግ ላይ ነው፡፡ ኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን የምትገኘው ቦቆጂ፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድር ከፍ ብላ እንድትጠራ ያስደረጉ ስመ ጥር ዓለም […]

የ2014 ቶታልኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አትሌቶች ውድድር በኢሌክትሪክ መኪና ይመራል፡፡

ጥር 9 ቀን 2014 ዓ.ም፡- ጥር 15 ቀን የሚካሄደው የ2014 ቶታልኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የወንድ እና ሴት አትሌቶች ውድድር በኢትየጵያ የኤሌክትሪክ መኪና በማስመጣት በሚታወቀው ግሪን ቴክ አማካኝነት በተዘጋጁ የኤሌክትሪክ መኪኖች የሚመራ እንደሆነ ታውቋል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በኤሌክትሪክ መኪና የሚደረገው የአትሌቶች እጀባ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በዘንድሮው አመት ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተዋወቀውን እና በ2014/15 የሚደረጉ ሁሉም ውድድሮች ላይ ግንዛቤ […]

የአትሌቶች 10ኪ.ሜ. ውድድር በግል ለሚሳተፉ 94 ያህል ተወዳዳሪዎች የማጣሪያ ውድድር በቅዳሜ መስከረም 29 ቀን አካሄደ፡፡

መስከረም 29 ቀን 2014 ዓ.ም. ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በ2014 ቶታልኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለሚካሄደው የአትሌቶች 10ኪ.ሜ. ውድድር በግል ለሚሳተፉ 94 ያህል ተወዳዳሪዎች የማጣሪያ ውድድር በቅዳሜ መስከረም 29 ቀን አካሄደ፡፡ ከባለፉት ሁለት አመታት ጀምሮ መደረግ የጀመረው የግል ተወዳዳሪ አትሌቶች የማጣሪያ ውድድር ዘንድሮ ለ3ተኛ ጊዜ ተካሂዷል፡፡ በዚህም ማጣሪያ ላይ ከአንድ እስከ ሶስት ለወጡ ተወዳዳሪዎች የማበረታቻ ገንዘብ ሽልማት […]

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከሶፊ ማልት ጋር የብራንድ አጋርነት ተፈራረመ፡፡

ሰኔ 4 ቀን 2013 ዓ.ም. ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግል ማህበር ዛሬ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ጥቁር ማልት ከሆነው እና ሙሉ በሙሉ ከተፈጥሮ ንጥረ- ነገሮች ከተሰራው ሶፊ ማልት ጋር የብራንድ አጋርነት ውል ተፈራረመ፡፡ የብራንድ አጋርነት ውል ፍርርሙ የተካሄደው ለ8 ሳምንታት በተካሄደው ለወርቅ ይነሱ ሩጫ ፕሮግራም ማጠናቀቂያ ላይ ነው፡፡ ይህ የብራንድ አጋርነት ፊርማ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በዓመት ውስጥ የሚያካሂዳቸውን […]

የሶፊ ማልት ወርቅ ሜዳልያ ያልሙ የሩጫ ልምምድ ፕሮግራም ዛሬ ተጀመረ::

ሰማንያ ተሳታፊዎች የተገኙበት የ8 ሳምንት የልምምድ ፕሮግራም የሆነው ከሶፊ ማልት ጋር ለወርቅ ይነሱ ፕሮግራም ዛሬ ጠዋት በያያ ቪሌጅ ተካሄደ፡፡ ተሳታፊዎች በሩጫ አለማማጅ አትሌቶች ታግዘው እንደአቅማቸው ከ4ኪ.ሜ እስከ 7ኪ.ሜ ሮጠዋል፡፡ የዚህ ፕሮግራም ዋና አላማ ተሳታፊዎች ሩጫን ለመለማመድ ከሚፈልጉ ሌሎች ተሳታፊዎች ጋር በመሆን የሩጫ ባህልን እንዲያዳብሩና መጀመሪያ ለማጠናቀቅ ያለሙትን ርቀት (20ኪ.ሜ፤ 30ኪ.ሜ ወይም 42ኪ.ሜ) በተያዘው ጊዜ ማጠናቀቅ […]