የ2015 ሶፊ ማልት ሀዋሳ ግማሽ ማራቶን ላይ ለሚሳተፉ አትሌቶች ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት ተዘጋጅቷል

ጥር 3 ቀን 2015 ዓ.ም.፡- እሁድ የካቲት 05 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚካሄደው የ2015 ሶፊ ማልት ሀዋሳ ግማሽ ማራቶን አትሌቶች ውድድር አጠቃላይ ከ400,000 ብር በላይ ሽልማት እንደሚሆን የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አዘጋጆች አሳወቁ። ሽልማቱ ውድድሩን (ግማሽ ማራቶኑን) ከ60 ደቂቃ በታች ለሚጨርሱ ማንኛውም ወንድ አትሌቶች እና ከ70 ደቂቃ በታች ለሚጨርሱ ሴት አትሌቶች በየዘርፋቸው የሚከፋፈሉት የ100,000 ብር ሽልማትን ያካትታል። […]

የ2015 ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ ዘመቻ የታቀደለትን ገቢ አሰባስቦ ለሶስት በጎ አድራጎት ድርጅቶች አስረከበ፡፡

በዘመቻው ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በተለያዩ መንገዶች ተሰብስቧል፡፡ ታህሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም.፡- ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ቢሮ ጋር በመተባበር የተለያዩ ማህበራትን ሲደግፍ የቆየው ሌሎችን ለመርዳት ሮጣለሁ ዘመቻ ዘንድሮም ሶስት የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን ታሳቢ ያደረገ የገቢ ማሰባሰቢያ ሲያደርግ እንደነበር ይታወቃል፡፡ የ2015 ሶፊ ማልት ቃላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. አካል የሆነው […]

የዝግታ ግማሽ ማራቶን ሯጩ ማስታወሻ ~ዳግም ተሾመ

የሃዋሳ ግማሽ ማራቶን ውድድር ሲጀመር ጀምሮ በአዘጋጅ ቡድን አባልነት ተሳትፌአለሁ፡፡ በተለያዩ አመታት የውድድሩ መንገድ ሲለካ አንዴም ባለ 3 ዙር አንዴም ባለ 2 ዙር ስለሚሆን ሙሉውን ግማሽ ማራቶን ሮጬው አላውቅም፡፡ ባለፈው አመት ግን የውድድሩ መንገድ አንድ ወጥ 21ኪ.ሜ. በመሆኑ መንገዱን ለመለካት ሙሉውን በሳይክል የመጓዝ እድሉ ነበረኝ፡፡ ነገር ግን ሳይክል መንዳት እና መሮጥ ለየቅል ናቸው፡፡ ውድድሩን ካካሄድን […]

የ2015 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ውድድር አካል የሆነው ሌሎችን ለመርዳት ሮጣለሁ የእርዳታ ማሰባሰብ ዘመቻ ያቀደውን 1 ሚልዮን ብር አሰባሰበ፡፡

ህዳር 5 ቀን 2015 ዓ.ም.፡- ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በመተባበር ሌሎችን ለመርዳት ሮጣለሁ አመታዊው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻ ዘንድሮ 1 ሚሊዮን ብር ለማሰባሰብ አቅዶ እየሰራ እንደነበር ይታወቃል፡፡ በየአመቱ እንደሚያደርገውም የተመረጡትን አክሽን ፎር ዴቨሎመንት (በድርቅ የተፈናቀሉ ወገኖች ላይ የሚሰራ)፤ ኢማጅን ዋን ደይ (ህፃናት ላይ የሚሰራ) እና ምዥዥጓ ሎካ የሴቶች ማጎልበቻ ማህበር ተጠቃሚዎች ያደርጋል፡፡ […]

ፔሬስ ጄፕቺርችር – የ2015 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ የክብር እንግዳ መሆኗ ታወቀ፡፡

ጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ.ም.፡- እ.ኤ.አየ2020 ቶኪዮ ኦሎምፒክ አሸናፊዋ ፔሬስጄፕቺርችር እሁድ ህዳር 11 ቀን በሚደረገው የ2015 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ ውድድር ላይ የክብር እንግዳ እንደምትሆን ታውቋል፡፡ የ29 አመቷ ፔሬስ በ2021 ባልተለመደ መልኩ የኒውዮርክ ማራቶንን እና የኦሎምፒክ አሸናፊነትን ያገኘች ሲሆን በ2022 ደግሞ በግሩም ብቃት የቦስተን ማራቶንን አሸንፋለች፡፡ ፔሬስ የ2016 እና የ2020 የሁለት […]

የ2015 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለምአቀፍ 10ኪሜ. አካል የሆነው የልጆች ሩጫ እና ሌሎችን ለመርዳት ሮጣለሁ የበጎ አድራጎት ዘመቻ ዛሬ በይፋ ይጀመራል፡፡

ጥቅምት 1 ቀን 2015 ዓ.ም.፡- 2015 ፕሌይማተርስ የህፃናት ሩጫ እና ሌሎችን ለመርዳት ሮጣለሁ የገቢ ማሰባሰቢያ መክፈቻ ጋዜጣዊ መግለጫ በዛሬው እለት ይካሄዳል፡፡ 40 ሺ ተሳታፊዎች የሚጠበቁበት እና ለ22ኛ ጊዜ የሚካሄደው ታላቁ ሩጫ ከሚካሄድበት እለት አንድ ቀን ቀደም ብሎ የሚካሄደው የህፃናት ውድድር ዘንድሮ ከ ፐሌይማተርስ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር የሚካሄድ ነው፡፡ የውድድሩም ዋና መልዕክት ከዚሁ ፕሮጀክት ጋር የተያያዘ […]

አዲስ አበባን የስፖርት ቱሪዝም መዳረሻ በማደረግ የሚገባትን ገፅታ ለማምጣት በስፖርትና መዝናኛ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ለመሥራት የሚያስችል ስምምነት ተካሄደ ።

ሰኔ 1፣ 2014 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ፣ በወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ እና በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መካከል በዛሬው እለት በከተማዋ እንደ ስፖርት ያሉ ቱሪስቶች የመሳብ አቅም ያላቸውን እንቅስቃሴዎች በጋራ በመተባበር፣ በማልማትና በማበልፅግ የስፖርት ቱሪዝምን እንዲስፋፋ ለመስራት የሶስትዮሽ ስምምነት ተፈራርመዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ ክብርት ዶክተር ሂሩት ካሳው፣ […]

እንጦጦ ፓርክ ፕሬዲተር ሩጫ – 7ኛ ዙር ውድድር በአዲስ አሸናፊነት ተጠናቀቀ!

እንጦጦ ፓርክ ፕሬዲተር ሩጫ – 7ኛ ዙር ውድድር በአዲስ አሸናፊነት ተጠናቀቀ! ቅዳሜ ነሃሴ 28 ቀን 2013 ዓ.ም. በተካሄደው የ7ተኛው ዙር እንጦጦ ፓርክ ፕሬደተር 5ኪ.ሜ. ሩጫ ላይ ሂክማ ሳባት እና ሃብታሙ አበራ አሸናፊዎች ሆነዋል፡፡ ውድድሩን ሃብታሙ አበራ በ17፡36፡58 ደቂቃ የጨረሰ ሲሆን ሂክማ ሳባት በ23፡27፡86 ደቂቃ አጠናቀዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በሚዲያዎች መካከል በተካሄደው ውድድር በወንዶች ታደሰ አብዩ ከብስራት […]

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሚዲያ አጋርነት ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሚዲያ አጋርነት ስምምነት ተፈራረሙ፡፡  “ባለፉት ሃያ ዓመታት ታላቁ ሩጫ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ማሰባሰብ ችሏል፧ በዓመት አንዴ ስለ ሰላም፣ ስለ ፍቅር፣ ስለ አብሮነት ልባቸውን እንዲሰጡ አድርጓል: በሐይማኖታዊ በዓላት አብረው መሆን ያልቻሉ ዜጎች በታላቁ ሩጫ ተቃቅፈው ይሮጣሉ፤ በብሔረሰባዊ መሰባሰቦች አንድ ላይ መሆን ያልቻሉ ሕዝቦች ታላቁ ሩጫን ጠብቀው […]

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የ 22ኛ ዙር ውድድር 40ሺ የመሮጫ ቦታዎች ውስጥ ግማሹን አገባደደ፡፡

ከተለያዩ ሃገራት የሚመጡ ተሳታፊዎችን ለማስተናገድ እየተዘጋጀ ያለው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የ 22ኛ ዙር ውድድር 40ሺ የመሮጫ ቦታዎች ውስጥ ግማሹን አገባደደ፡፡ የ2015 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለምአቀፍ 10ኪ.ሜ. ለ22ኛ ጊዜ ሊካሄድ ዝግጅት ተጀምሯል፡፡ትምህርት ለሁሉም ህፃናት የዘንድሮ የሩጫ መልዕክት ነው፡፡ዘንድሮ 40ሺ ተሳታፊዎች የሚሳተፉ ሲሆን ይህ ቁጥር ባለፉት 2 አመታት በነበረው ወረርሽኝ ምክንያት ቀንሶ የነበረውን ተሳታፊ ቁጥር […]