300 ሰዎች በላይ በተለያዩ የአለማችን ክፍል የሚኖሩ ተሳታፊዎች የ2014 ቶታልኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. ውድድር ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 5 ቀን አካሂደዋል፡፡

Share This Post

Share on facebook
Share on linkedin
Share on twitter
Share on email

የ2014 ቶታልኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. ውድድር ላልተወሰነ ጊዜ ቢራዘምም ከ300 ሰዎች በላይ በተለያዩ የአለማችን ክፍል የሚኖሩ ተሳታፊዎች በያሉበት ሆነው የግል ሩጫቸውን ባሳለፍነው ሳምንት ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 5 ቀን አካሂደዋል፡፡

በዚህ ውድድር ላይ 10 የሚሆኑ ሃገራትን የወከሉ ተወዳዳሪዎች ተሳታፊዎች ሆነዋል፤ ተሳፊዎች ያሳለፉትን ሩጫ በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ማህበራዊ ገፆች ላይ @GreathEthRun (ትዊተር) ወይም / @GreatEthiopianRun (ፌስቡክ) ላይ መመልከት ይቻላል፡፡

በሊድስ- ዮርክሸር የሚገኘው አቤ ግራንች ኢንግላንድ ቤተ-ክርስቲያን አካዳሚ ተማሪዎች በቁጥራቸው ትልቅ ሆነው የተሳተፉ ሲሆን፤ ይህ ትምህርት ቤት በቀደሙ አመታት ተሳታፊዎችን ወደ አዲስ አበባ በመላክ አሳታፊ በማድረግም የሚታወቅ መሆኑ ተገልጧል፡፡

በእንግሊዝ አገር የሚኖሩ 40 የሚደርሱ ኢትዮጵያውያንም በዘንድሮው ውድድር ላይ ተሳታፊዎች ሆነዋል፤ ከዚህም በተጨማሪ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድር አዘጋጆችም የውድድሩን ቀን ለማክበር ተሰባስበው የውድድሩ መስመር ላይ ህዳር 5 ቀን ሮጠዋል፡፡

More To Explore

10KM

የ2015 ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ ዘመቻ የታቀደለትን ገቢ አሰባስቦ ለሶስት በጎ አድራጎት ድርጅቶች አስረከበ፡፡

በዘመቻው ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በተለያዩ መንገዶች ተሰብስቧል፡፡ ታህሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም.፡- ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ቢሮ ጋር በመተባበር የተለያዩ