ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ. በ”RUNNERS WORLD” ምርጥ 10ኪሜ ሩጫዎች ዝርዝር ውስጥ ተቀዳሚውን ቦታ አግኝቷል፡፡
ግንቦት 09 ቀን 2014 ዓ.ም. – ለ21 አመታት ያለመቋረጥ የተካሄደው እና ለበርካታ አትሌቶች የመፎካከሪያ መድረክ በመፍጠር ተቀዳሚ ቦታን የያዘው አመታዊው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል 10ኪሜ ውድድር በየወሩ የሚወጣው ራነርስ ወርልድ መፅሄት በዚህ ወር ዝርዝሩ ላይ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በአለም ላይ ካሉ ታዋቂ የ10ኪሜ ውድድሮች ውስጥ በቀዳሚነት ተጠቃሽ ነው ሲል አስፍሮታል፡፡ ራነርስ ወርልድ የተለያዩ የሩጫ ዜናዎችን፤ የስልጠና ጠቃሚ መልእልቶችን፤ […]
የአይኤፍኤች ኢንጂነሪንግ 20ኛ አመት የምስረታ በአል ከሳርቤት እስከ ጎተራ በዱላ ቅብብል ውድድር ሊያከብር ነው
አይኤፍኤች ኢንጂነሪንግ (በቀድሞ ስሙ ‘ሲአርቢሲ አዲስ ኢንጂነሪንግ’ ተብሎ ይንቀሳቀስ የነበረው) እሁድ ሐምሌ 10 ቀን 2014 የሚካሄደውን የ2014 የአይኤፍኤች የዱላ ቅብብል ስፖንሰር በማድረግበኢትዮጵያ የ20 ዓመታት ስራውን ያከብራል። ውድድሩ የሚካሄደው በአይኤፍኤች በተጠናቀቀው ከሳርቤት ፑሽኪን አደባባይ ወደጎተራ ማሳለጫ መንገድ ከአዲስ አበባ በደቡብ በኩል ባለው አዲስ መንገድ ላይ ነው። አይኤፍኤች ኢንጂነሪንግ እነዚህን የዱላ ቅብብሎሽ ለመጀመሪያ ጊዜ ስፖንሰር ያደረገው በ 1997 ዓ.ም ከቃሊታ እስከ መገናኛ ባለው የአዲስ አበባ ቀለበት መንገድ ምስራቃዊ ዝርጋታ መጠናቀቁን ምክንያት በማድረግ ነበር። በ1999 ለሦስተኛ ጊዜ በድጋሚ ከተካሄደው የዱላ ቅብብል ውድድር በኋላ ኩባንያው ከአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን (አአአክራ) ጋር በመተባበር ዝግጅቱን በከተማዋ ወደሚገኙ ሌሎች ቦታዎች ተዘዋውሮ ባስገነባቸው ሌሎች አዳዲስ መንገዶች ላይ አክብርዋል። በቅርብ ጊዜ የተካሄደው፣ 16 ኛው ተከታታይ አመታዊ የዱላ ቅብብል ውድድር፣ የተካሄደው ከሦስት ዓመታት በፊት በ 2011 የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከመከሰቱ በፊት ነበር። ባለፉት ሃያ ዓመታት አይኤፍኤች ኢንጂነሪንግ የመንገድና ድልድይ ግንባታ ፕሮጀክቶቹን ባከናወነበት ፍጥነት መልካም ስም አትርፏል። ከፕሮጀክቶቹ መካከል የአዲስ አበባ ቀለበት መንገድ፣ የኢትዮ-ቻይና ወዳጅነት መንገድ በወሎ ሰፈር፣ የቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ማኮብኮቢያ ማሻሻያና ማስፋፊያ ፕሮጀክት፣ ከመገናኛ እስከ አያት መንገድ፣ ከመገናኛ እስከ ጦርኃይሎች መንገድ፣ ከመስቀል አደባባይ እስከ ቃሊቲ መንገድ ድረስ ያሉ ፕሮጀክቶች ይገኙበታል። […]
ሶፊ ማልት በአፍሪካ ትልቁ የሆነውን የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ስያሜ ወሰደ
ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም. የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አዘጋጆች ህዳር 11 ቀን 2015 ዓ.ም. ለ22ኛ ጊዜ ለሚያካሂዱት ውድድር የስያሜ ስፖንሰር ሶፊ ማልት መሆኑን አሳውቀዋል፡፡ ሄኒከን ኢትዮጵያ በሶፊ ማልት ምርቱ ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር ከዚህም በተጨማሪ የተለያዩ ውድድሮች ላይ በአጋርነት ይሰራል፡፡ ሳምራዊት ግርማ የሄኒከን ስፖንሰርሽፕ እና ብራንድ ማናጀር የዚህ ስምምነት መጠናቀቅን አስመልክተው “በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሚዘጋጁ […]