ለ2014 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5 ኪሜ ውድድር 10,000 ሴቶች ለውድድሩ ተመዘገቡ፡፡

የ2014 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5 ኪሜ ውድድር አዘጋጆች ዛሬ ይፋ እንዳደረጉት የፊታችን እሁድ መጋቢት 13 ቀን 2014 ዓ.ም. ለሚካሄደው ውድድር አስር ሺህ ቲሸርቶች መሸጣቸውን አስታውቀዋል። በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በ2000 ተሳታፊ ብቻ ተወስኖ የነበረው ውድድር ወደ ነበረበት የተሳታፊ መጠን ይመለሳል :: “ከሁለት አመት በፊት ከደረስንበት የተሳታፊ መጠን ላይ መድረስ በጣም አስደሳች ነው” ሲሉ የተናገሩት የታላቁሩጫ በኢትዮጵያ […]