ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በየወሩ በእንጦጦ ፓርክ የሚደረገውን የ5ኪ.ሜ. ውድድር በይፋ አስጀመረ።

የተሳታፊዎችን የሩጫ ውድድር ፍላጎትና ጤናማ አኗኗር ባህል የማድረግ ፍላጎት መጨመርን ታሳቢ በማድረግ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በየወሩ የሚካሄድ 5ኪ.ሜ. ውድድርን እንደሚጀምር በዛሬው እለት በይፋ አስታውቋል፡፡ ውድድሩ በአዲሱ እና ለስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ተስማሚ በሆነው የእንጦጦ ፓርክ ይካሄዳል፡፡ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ወር በገባ የመጀመሪያ ቅዳሜ በየወሩ የሚደረገው ይህ ውድድር የመጀመሪያው ዙር የፊታችን ጥር 29 ቀን 2013 ኣ.ም. ይካሄዳል፡፡ የዚህንም ፕሮግራም […]