ራእይ አማን እና ሃብታሙ አበራ በአምስተኛው ዙር እንጦጦ ፓርክ ፕሬደተር ሩጫ ለሁለት ተከታታይ ወራት አሸናፊ ሆኑ፡፡

ሰኔ 26 ቀን 2013 ዓ.ም. የግንቦት ወር አሸናፊ የነበሩት የ13 አመቱዋ ራእይ አማን እና ሃብታሙ አበራ ለሁለተኛ ጊዜ በተከታታይ አሸናፊ ሆነዋል፡፡ ራእይ አማን በ25፡41፡92 ሩጫዋን ከባለፈው ወር ኣሻሽላለች፡፡ ሃብታሙ አበራ በ18፡14፡17 ሩጫውን አሻሽሏል፡፡ በዚሁ እለት ውድድር ላይ በሴቶች አቢጊያ ሰለሞን እና የግሌ እሸቱ በወንዶች ደግሞ አብዱራዛቅ አለዊ እና ምህረት አበራ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሆነው አጠናቀዋል፡፡ […]