የ2013 ሶፊ ማልት ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ ሩጫ የኢትዮጵያ ሴቶችን ስኬት እናክብር በሚል መርህ ተካሄደ::

ሶፊ ማልት ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ ሩጫ የኮሮና ቫይረስን ቅድመ ሁኔታዎች ባገናዘበ መልኩ በዛሬው እለት በ2000 ተሳታፊዎች ብቻ ተካሄዷል፡፡ በውድድሩ ላይ የተከበሩ ወ/ሮ ፊልሰን አብዱላኪ የሴቶች፤ ህፃናትና ወጣቶች ሚንስቴር ሚንስትር የተገኙ ሲሆን ሴቶች ኢትዮጵያዊነትን በልባቸው ይዘው ለተሻለ ነገ እንዲተጉ አስታውሰዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አትሌት ሃይሌ ገ/ስላሴና አትሌት መሰረት ደፋር በውድድሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉ ሲሆን አትሌት አሰለፈች […]