የእንጦጦ ፓርክ ፕሬዴተር ሩጫ ተራዘመ

ጥር 29 ቀን 2013 ኣ.ም. የሚደረገው የእንጦጦ ፓርክ ፕሬደተር ሩጫ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት የተራዘመ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ የዚህ ወርሃዊ ውድድር ለ200 ተሳታፊዎች ብቻ እንደሚደረግ የሚታወቅ ሲሆን የጥር ወር ተሳታፊዎች ምዝገባቸው ተጠብቆ ውድድሩ የሚካሄድበት ተለዋጭ ቀን ላይ የውድድሩ ተካፋይ እንዲሆኑ አስቀድመን የምናሳውቅ መሆናችንን በትህትና እንገልፃለን፡፡