ስፖርት እና ማህበረሰብ

ቀለል ያለው አለባበሱ በስፖርት የዳበረ ሰውነቱን ባይደብቅበትም ስፖርተኞቹን መቀላቀል አልፈለገም፡፡ የ39 ዓመቱ ውብሸት መንግስቱ ጥግ ይዞ አድፍጧል፡፡  የሀዋሳ ግማሽ ማራቶን በተካሄደበት ባለፈው የሚያዚያ አጋማሽ እሁድ ጠዋት አስቀድመው “ገብርኤል አደባባይ” አቅራቢያ የተሰባሰቡትን ሯጮች በተመስጦ ይመለከታል፡፡ “ታውቃለህ… ከሯጮቹ የማውቀው ሰው አላየሁም” ይላል በመገረም የአንድ እጁን መዳፍ አፉ ላይ ጭኖ፡፡ የእድሜውን ሶስት አራተኛ በሀዋሳ የኖረው ውብሸት እንደ ቀደመው […]