የጃኖዎቹ – ሔዋንና ሃሌሉያ

ሔዋን ትሮጣለች፡፡ ድምጻዊት እንደመሆንዋ በተለይ የመንገድ ሩጫን እንደ ጥሩ ትንፋሽ ማስተካከያ ትጠቀምበታለች፡፡ ሙዚቃ እየሰማች እስከ 6ኪሎ ሜትር ትሮጣለች፡፡ አካላዊ ብርታትዋን እና ጥንካሬዋን ለመጠበቅ ደግሞ ወደ ጂም ትሄዳለች፡፡ “በይበልጥ ግን መንገድ ላይ የምሮጠው ይበልጣል” ትላለች፡፡ ጃኖ ከመጀመሯ ቀደም ባለው ጊዜ እንዲያውም ክብደቷን ለመቆጣጠር እና በሌሎችም ምክንያቶች በሳምንት ሰባቱን ቀናት የምትሰራበት ጊዜ ነበር፡፡ “ስቴጅ ላይ ትንፋሽ ያስፈልጋል፡፡ […]