ኢትዮጵያ እና ሩጫ

የ19 አመቷ ዮዲት ፓልመር (ስሟ የተቀየረ) በአሜሪካ ሀገር ትኖራለች፡፡  ገና በአራት አመቷ በጉዲፈቻ ከሀገሯ የወጣችው ወጣት አማርኛ ቋንቋ አትናገርም፡፡ አትሰማምም፡፡ ሆኖም በኢንተርኔት ስለ ኢትዮጵያ ለማወቅ ትሞክራለች፡፡ በአጋጣሚዎች ሁሉ ስለ ኢትዮጵያ እያነሳች አሜሪካዊያን ጓደኞቿ ስለ ሀገሯ የሚያውቁትን ለመስማት ትፈልጋለች፡፡  ካወራቻቸው በቁጥር የበዙት “ኢትዮጵያውያን ሯጮች ናቸው” ይሏታል፡፡ የሀይሌ ገ/ስላሴን እና ሌሎችንም ታላላቅ አትሌቶች ስም እያስታወሱ ይነግሯታል፡፡ “በዜግነቴ […]