ታላቁ ሩጫ ላይ ያላሸነፍኩባቸው አምስት ሰበቦች (ሎል

ታላቁ ሩጫ እንደ እንቁጣጣሽ የሕዝብ በዓል መሆኑ ሁሌም ሲደርስ ብቻ ነው የሚገባኝ፡፡ የዘንድሮው ትኬት በአንድ ሳምንት ተሸጦ በማለቁ፣ ከአትራፊዎች ለመግዛት ያላየነው ፍዳ አልነበረም – ደግነቱ ተሳክቷል፡፡ ነገር ግን ‹‹እንደተጠበቅኩት›› አንደኛ ሳልወጣ ቀርቼያለሁ፡፡ ሰበብ አለኝ፡፡ ምናልባት እናንተ ግምታችሁን ስትሰነዝሩ ‹‹ጫማው ስለጠበበው፣ በዋዜማው የበላው እራት ስላልተስማማው፣ ውድድሩ በተጀመረ ሰባተኛው ደቂቃ ላይ ሆድ ቁርጠት ስለጀመረው፣ የዳኞች አድሎ ስለነበር….›› […]