ፔሬስ ጄፕቺርችር – የ2015 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ የክብር እንግዳ መሆኗ ታወቀ፡፡

Share This Post

Share on facebook
Share on linkedin
Share on twitter
Share on email
የ2020 ቶኪዮ ኦሎምፒክ አሸናፊዋ ፔሬስ ጄፕቺርችር

ጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ.ም.፡- እ.ኤ.አየ2020 ቶኪዮ ኦሎምፒክ አሸናፊዋ ፔሬስጄፕቺርችር እሁድ ህዳር 11 ቀን በሚደረገው የ2015 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ ውድድር ላይ የክብር እንግዳ እንደምትሆን ታውቋል፡፡

የ29 አመቷ ፔሬስ በ2021 ባልተለመደ መልኩ የኒውዮርክ ማራቶንን እና የኦሎምፒክ አሸናፊነትን ያገኘች ሲሆን በ2022 ደግሞ በግሩም ብቃት የቦስተን ማራቶንን አሸንፋለች፡፡

ፔሬስ የ2016 እና የ2020 የሁለት ጊዜ የአለም ግማሽ ማራቶን አሸናፊም የሆነችው ፔሬስ ፈጣን የማራቶን ሰዓቷ የሆነውን 2 ሰዓት ከ17 ደቂቃ ከ16 ሰከንድ በቫሌንሽያ ከሁለት አመት በፊት አስመዝግባለች፡፡ ከታዋቂ የኢትዮጵያ አትሌቶችም ጋር በመፎካከር የምትታወቅ ሲሆን አብራቸው ከተሳታፈቻቸው አትሌቶች ውስጥ ያለምዘርፍ የኃሏው፤ ደጊቱ አዝመራው፤ ነፃነት ጉደታ እና ዘይነባ ይመር ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ፔሬስ ጄፕቺርችርከኬንያ አብረዋት በዘንድሮው ውድድር ለመሳተፍ የሚመጡ አትሌቶችም ይኖራሉ፡፡ በተጨማሪ ከተለያዩ የኬንያ መገናኛ ብዙሃን የሚመጡ ጋዜጠኞች ይኖራሉ፡፡

በዘንድሮው ውድድር ላይ ከአትሌት ሻለቃ ሃይሌ ገ/ስላሴ ጋር በ1993 የስቱትጋርት የአለም ሻምፒዮና ላይ ታሪካዊ የ10,000 ሜትር ውድድር ያደረገው ኬንያዊው አትሌት ሞሰስ ታኑይ የሚገኝ ይሆናል፡፡ ሞሰስ ታኑይ የኤልዶሬት ከተማ ማራቶን ውድድር ዋና አዘጋጅ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ወደ ኢትዮጵያ ስትመጣ የመጀመሪያዋ የሚሆነው ፔሬስ አርብ ህዳር 10 ጠዋት በሃያት ሬጀንሲ ከሚደረገው የመጨረሻ ጋዜጣዊ መግለጫ ጀምሮ እስከ ውድድሩ ቀን ድረስ ለመቆየት ከባለቤቷ እና ልጇ ጋር የምትገኝ ይሆናል፡፡

ለበለጠ መረጃ በ0911601710 ወይም hilina@ethiopianrun.org ሕሊና ንጉሴ ብለው ይጠይቁ፡፡

More To Explore

10KM

የ2015 ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ ዘመቻ የታቀደለትን ገቢ አሰባስቦ ለሶስት በጎ አድራጎት ድርጅቶች አስረከበ፡፡

በዘመቻው ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በተለያዩ መንገዶች ተሰብስቧል፡፡ ታህሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም.፡- ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ቢሮ ጋር በመተባበር የተለያዩ