ዶ/ር ሴቶር ኖርግቤ በ2014 ቶታልኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል 10ኪ.ሜ. ላይ ተሳታፊ ትሆናለች፡፡

Share This Post

Share on facebook
Share on linkedin
Share on twitter
Share on email

ዶ/ር ሴቶር ኖርግቤ በ2014 ቶታልኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል 10ኪ.ሜ. ላይ ተሳታፊ ትሆናለች፡፡

ታህሳስ 06 2014 ዓ.ም. ፡- የጋና የ2021 የቁንጅና ውድድር በጣም ቆንጆ አሸናፊ እና ስለ አፍሪካ አንድነት ጠንካራ አቀንቃኝ ዶ/ር ሴቶር ኖርግቤ እሁድ ጥር 15 ቀን በ2014 ቶታልኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ላይ ተሳታፊ እንደምትሆን ታውቋል፡፡

ሩጫው ላይ ከመሳተፍም በተጨማሪ አርብ ጥር 13 ቀን 2014ዓ.ም. በሚካሄደው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይም በክብር እንግድነት የምትገኝ ይሆናል፡፡

የህክምና ዶክተሩዋ ዶ/ር ሴቶር ኖርግቤ ላለፉት 2 ሳምንታት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በመንቀሳቀስ የተለያዩ የኢትዮጵያ ባህልን ለመታደም ችላለች፡፡

ዶ/ር ሴቶር በኢትዮጵያ ያላትን ቆይታ ከውድድሩ በፊት ለማጠናቀቅ አስባ የመጣች የነበር ቢሆንም ስለውድድሩ ከሰማች እና አትሌት ሃይሌ ገ/ስላሴን ለማግኘት እንደምትችል ካወቀች በኃላ የጉዞ ቆይታዋን አራዝማለች፡፡

ስለ2014 ቶታልኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተጨማሪ መረጃ ከዛሬ ጀምሮ በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ድረ-ገፅ እና ማህበራዊ ገፅ ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡

ለበለጠ መረጃ www.ethiopianrun.org/en/news/press-releases

ወይም ሕሊና ንጉሴ hilina@ethiopianrun.org

More To Explore

10KM

የ2015 ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ ዘመቻ የታቀደለትን ገቢ አሰባስቦ ለሶስት በጎ አድራጎት ድርጅቶች አስረከበ፡፡

በዘመቻው ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በተለያዩ መንገዶች ተሰብስቧል፡፡ ታህሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም.፡- ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ቢሮ ጋር በመተባበር የተለያዩ