የ2015 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለምአቀፍ 10ኪሜ. አካል የሆነው የልጆች ሩጫ እና ሌሎችን ለመርዳት ሮጣለሁ የበጎ አድራጎት ዘመቻ ዛሬ በይፋ ይጀመራል፡፡

Share This Post

Share on facebook
Share on linkedin
Share on twitter
Share on email

ጥቅምት 1 ቀን 2015 ዓ.ም.፡-

2015 ፕሌይማተርስ የህፃናት ሩጫ እና ሌሎችን ለመርዳት ሮጣለሁ የገቢ ማሰባሰቢያ መክፈቻ ጋዜጣዊ መግለጫ በዛሬው እለት ይካሄዳል፡፡ 40 ሺ ተሳታፊዎች የሚጠበቁበት እና ለ22ኛ ጊዜ የሚካሄደው ታላቁ ሩጫ ከሚካሄድበት እለት አንድ ቀን ቀደም ብሎ የሚካሄደው የህፃናት ውድድር ዘንድሮ ከ ፐሌይማተርስ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር የሚካሄድ ነው፡፡

የውድድሩም ዋና መልዕክት ከዚሁ ፕሮጀክት ጋር የተያያዘ እና ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከክልል የት/ቤት ቢሮዎች ጋር በጋራ ለመምህራን በተማሪ ተኮር የማስተማር ስነ-ዘዴ ላይ የሙያዊ እድገት እድል ለመስጠት እየሰራ የሚገኝ ፕሮጀት ነው፡፡ ይኸውም  በስልጠና፤ ት/ትን ሲሰጡ የሚጠቀሙአቸውን የማስተማሪያ ሰነዶች በጋራ በመቅረፅ፤ ቀጣይነት ያለው ማስተማር እንዲሁም መምህራን ልምድ እንዲለዋወጡ እና እርስ በእርስ እንዲማማሩ የሚያስችሉ የአቻ ድጋፍ መድረኮችን በማዘጋጀት ነው፡፡ፕሌይ ማተርስ ፕሮጀክት ተማሪ ተኮር የማስተማር ስነ ዘዴን በመጠቀም የስደተኞች እና የተቀባይ ማህበረሰቡን ልጆች አጠቃላይ ትምህርትን፤ደህንነትን እና እድገትን ለማሻሻል ይፈልጋል፡፡ ፕሌይ ማተርስ በኢትዮጵያ ውስጥ በጋምቤላ፣ በቤኒሻንጉል፣ በአፋር እና በሱማሌ ክልል በስደተኛ ካምፖች እና በማህበረሰቡ ውስጥ ላለፉት ሁለት አመታት ሲተገብር ቆይቷል፡፡

 ከዚህም በተጨማሪ በዛሬው እለት የተጀመረው ሌሎችን ለመርዳት ሮጣለሁ ዘመቻ በዘንድሮ አመትም ልክ እንደወትሮው ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ቢሮ ጋር በመተባበር 3 የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የተመረጡ ሲሆን እነሱም አክሽን ፎር ዴቨሎመንት፤ አክሽን ፎር ዴቨሎፕመንት እና ምሽሽገዋ ሎካ የሴቶች ማጎልበቻ ማህበር ናቸው፡፡

ምንም እንኳን የቀጣዩን ውድድር መሳተፊያ ቲ-ሸርት ሽያጭ ቀደም ብሎ ያለቀ ቢሆንም የዚህን ሌሎችን ለመርዳት ሮጣለሁን ዘመቻ ለመርዳት ይሆን ዘንድ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የተወሰኑ ቲ-ሸርቶችን አስቀርቶ ለሽያጭ አዘጋጅቷል፡፡ ምዝገባ ያለፋቸው ተሳታፊዎችም ይህን እድል ተጠቅመው ሩጫቸው ሌሎችን እንዲረዱ እንዲሆን ታላቁ ሩጫ ጥሩውን ያቀርባል፡፡ 

የ2015 ፕለይማተርስ የህፃናት ሩጫ ቲ-ሸርት ሽያጭ ከጥቅምት 2 ቀን ጀምሮ በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ቢሮ የሚጀመር ሲሆን የቲ-ሸርት እና ውድድሩን ሲያጠናቅቁ የሚሰጣቸውን ሜዳልያ ጨምሮ 250 የመመዝገቢያ ዋጋው 0ይሆናል፡፡ ለበለጠ መረጃ የማርኬቲንግ እና ኮሚኑኬሽን ዳይሬክተር ህሊና ንጉሴን በhilina@ethiopianrun.org በ0911601710 ያግኙ፡፡

More To Explore

10KM

የ2015 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ውድድር አካል የሆነው ሌሎችን ለመርዳት ሮጣለሁ የእርዳታ ማሰባሰብ ዘመቻ ያቀደውን 1 ሚልዮን ብር አሰባሰበ፡፡

ህዳር 5 ቀን 2015 ዓ.ም.፡- ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በመተባበር ሌሎችን ለመርዳት ሮጣለሁ አመታዊው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻ ዘንድሮ 1 ሚሊዮን ብር