የ2014 ቶታልኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አትሌቶች ውድድር በኢሌክትሪክ መኪና ይመራል፡፡

Share This Post

Share on facebook
Share on linkedin
Share on twitter
Share on email

ጥር 9 ቀን 2014 ዓ.ም፡- ጥር 15 ቀን የሚካሄደው የ2014 ቶታልኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የወንድ እና ሴት አትሌቶች ውድድር በኢትየጵያ የኤሌክትሪክ መኪና በማስመጣት በሚታወቀው ግሪን ቴክ አማካኝነት በተዘጋጁ የኤሌክትሪክ መኪኖች የሚመራ እንደሆነ ታውቋል፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ በኤሌክትሪክ መኪና የሚደረገው የአትሌቶች እጀባ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በዘንድሮው አመት ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተዋወቀውን እና በ2014/15 የሚደረጉ ሁሉም ውድድሮች ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ የሚሰራበትን የአረንጓዴ ሩጫ አምስት መሰረታዊ መርሆዎች አንዱ የሆነውን የካርበን ልቀትን በተቻለ መጠን መቀነስ ለማበረታታት ነው፡፡

የውድድሩ መልእክት የሆነው እና በዩኒሴፍ የተዘጋጀው መፀዳዳት በሽንት ቤት ከዚህ አረንጓዴ ሩጫ ጋርም ተያያዥነት ይኖረዋል፡፡

“ወደ 22 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ያለመፀዳጃ ቤት ይፀዳዳሉ” ያሉት በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ ተወካይ ጂያንፍራንኮ ሮቲሊያኖ፤ “የንፅህና ጉድለትና ያለሽንት ቤት መፀዳዳት የማህበራዊ ጤና ላይ በተለይም ለህፃናት ከፍተኛ ተፅእኖ ያስከትላል፡፡ እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት ቀዳሚ ገዳይ በሽታ የሆነው የተቅማጥ በሽታም በዚሁ ምክንያት ከሚመጡ ችግሮች ውስጥ ተጠቃሽ ነው፡፡ ዛሬ ህፃናት ያለ መፀዳጃ ቤት በመፀዳዳት ከሚመጣባቸው እልፈተ ህይወት ታድገን ጤናማ ህይወት እንዲመሩ የለውጥ አጋርነታችንን በጋራ አንድናሳይ ለሁላችሁም ጥሪ እናቀርባለን” ብለዋል፡፡

ከዚህም ጋር ተያይዞ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከተለያዩ የሩጫ አጋሮች ጋር በመተባበር የፊታችን ቅዳሜ የመሮጫ መንገዱ ላይ በተለይም ሶስት ቦታዎችን መርጦ የፅዳት ስራ የሚሰራ ይሆናል፡፡ በዚህ የፅዳት ፕሮግራም ላይ ቶታልኢነርጂስ፤ ሶፊ ማልት፤ ዩኒሴፍ፤ ሃያት ሬጀንሲ እና አርኪ ውሃ ከፔትኮ የፅዳት ሰራተኞች ጋር በመተባበር የሚያፀዱ ይሆናል፡፡

“ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሀገራችን ውስጥ ከሚደረጉ የሩጫ ዝግጅቶች ትልቁ ከመሆኑ አንፃር ሁሌም ማህበረሰባዊ ሃላፊነቶችን ለመወጣት ይሰራል” ያሉት የማርኬቲንግ ዳይሬክተሯ ሕሊና ንጉሴ “ይህ ጅማሮ ሌሎችም እንዲከተሉት የሚያበረታታ እንደሚሆን እምነታችን ነው” ብለዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ www.ethiopianrun.org/en/news/press-releases

ወይም hilina@ethiopianrun.org ስልክ፡ 0911601710

More To Explore

10KM

የ2015 ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ ዘመቻ የታቀደለትን ገቢ አሰባስቦ ለሶስት በጎ አድራጎት ድርጅቶች አስረከበ፡፡

በዘመቻው ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በተለያዩ መንገዶች ተሰብስቧል፡፡ ታህሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም.፡- ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ቢሮ ጋር በመተባበር የተለያዩ