የ2014 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ምዝገባ ሰኞ የካቲት 7 ቀን ይጀመራል፡፡

Share This Post

Share on facebook
Share on linkedin
Share on twitter
Share on email

ጥር 3 ቀን 2014 ዓ.ም. ፡- ከ18 አመት በፊት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የክልል ውድድር እና የመጀመሪያውን የቅድሚያ ለሴቶች ውድድር ለማዘጋጀት አቅዶ ተዘጋጀ፡፡ የመጀመሪያው የቅድሚያ ለሴቶች 5ኪሜ ሩጫ በግንቦት ወር 1994 ዓ.ም. ተደረገ፡፡

ከ18 አመታት በኃላ የዛሬ 18 አመት ታላቁ ሩጫን የተቀላቀለችው ዳግማዊት አማረ በስራ አስኪያጅነት እየመራች የ19ኛውን ዙር የቅድሚያ ለሴቶች ውድድር ለማድረግ የምዝገባ መክፈቻውን ማሳወቂያ ቀን ላይ ደርሳለች፡፡

ሳፋሪኮም የስያሜ ስፖንሰር እንደሚሆን ከሳምንት በፊት የታወቀው ይህ ውድድር 10000 ተሳታፊዎችን እንደሚያሳትፍ ታውቋል፡ የዘንድሮው ውድድር መልዕክት “የኢንተርኔት ደህንነት ለህዳናትና ለሴቶች’’ የሚል ሲሆን በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የተገኙት የህፃናት ፕሮቴክሽን ኦፊሰር ኢን ቻርጅ የሆኑት አሚኑል ኢዝላም እንደተናገሩት ‘’ዩኒሴፍ ኢንተርኔት ለተጠቃሚዮች በተለይም ከህጻናት እና ሴቶች አመቺ እንዲሆን አየሰራ ይገኛል፡፡ ሴቶችና ህፃናት ኢንተርኔት ተጠቅመው የበለጠ እንዲማሩ፤ ከሰዎች ጋር እንዲግባቡና እራሳቸውን እንዲገልፁ ያበረታታል፡፡’’ ብለዋል

በውድድሩ ምዝገባ መክፈቻ ላይ ዳግማዊት አማረ ‘’ውድድሩን በተለያዩ ተግዳሮቶች ውስጥም ሆነን ሳናቋርጥ ማድረግ በመቻላችን በጣም እድለኞች ነን፤ እንደሚታወሰው የ17ተኛው ዙር ውድድር ኮቪድ 19 ወደ ሃገሪቱ እንደገባ የተደረገ ሲሆን፤ የባለፈው አመቱን በጣም ውስን በሆነ ተሳታፊ እና መሰረታዊ የኮቪድ ጥንቃቄዎችን በማድረግ የተደረገ ውድድር እንደነበር ተናግረዋል’’፡፡

በአጠቃላይ የመቶ ሺ ብር ሽልማት በአትሌቶች ውድድር ለሚያሸንፉ ተወዳዳሪዎች የሚሸልመው ይህ ውድድር አንደኛ ለሚወጡ የ25 ሺ ብር ሽልማትን ያበረክታል፡፡ በዚህ ውድድር ካሸነፉ አትሌቶች ውስጥ ያለምዘርፍ የኃላው፤ ፀሃዬ ገመቹና ፅጌ ገብረሰላማ ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ማስታወሻ፡- የ2014 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች መመዝገቢያ ዋጋ 300 ብር ነው፡፡ የዘንድሮው ውድድር መጋቢት 4 ቀን ይካሄዳል፡፡ ውድድሩ በተለመደው አትላስ አካባቢ ይካሄዳል፡፡ የሶፊ ማልት 4 ሳምንት የልምምድ ፕሮግራም ፈቃደኛ ለሆኑ ሴት ራጮች እሁድ የካቲት 6 ይጀመራል፡፡

የምዝገባ ማስከፈቻ ጋዜጣዊ መግለጫ ሙሉ መረጃ ከዚህ ኢሜል ጋር አያይዘን ልከናል፡፡ ምዝገባው የፊታችን ሰኞ የካቲት 7 ቀን በ3 የእናት ባንክ ቅርንጫፎች ማለትም በካዛንችስ፤ በሚክሲኮ እና መገናኛ እንዲሁም በታላቁ ሩጫ ቢሮ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

ለበለጠ መረጃ www.ethiopianrun.org/en/races/women-first-5km ወይም hilina@ethiopianrun.org

More To Explore

10KM

የ2015 ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ ዘመቻ የታቀደለትን ገቢ አሰባስቦ ለሶስት በጎ አድራጎት ድርጅቶች አስረከበ፡፡

በዘመቻው ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በተለያዩ መንገዶች ተሰብስቧል፡፡ ታህሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም.፡- ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ቢሮ ጋር በመተባበር የተለያዩ