የ2013 ሶፊ ማልት ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ ሩጫ የኢትዮጵያ ሴቶችን ስኬት እናክብር በሚል መርህ ተካሄደ::

Share This Post

Share on facebook
Share on linkedin
Share on twitter
Share on email

ሶፊ ማልት ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ ሩጫ የኮሮና ቫይረስን ቅድመ ሁኔታዎች ባገናዘበ መልኩ በዛሬው እለት በ2000 ተሳታፊዎች ብቻ ተካሄዷል፡፡

በውድድሩ ላይ የተከበሩ ወ/ሮ ፊልሰን አብዱላኪ የሴቶች፤ ህፃናትና ወጣቶች ሚንስቴር ሚንስትር የተገኙ ሲሆን ሴቶች ኢትዮጵያዊነትን በልባቸው ይዘው ለተሻለ ነገ እንዲተጉ አስታውሰዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አትሌት ሃይሌ ገ/ስላሴና አትሌት መሰረት ደፋር በውድድሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉ ሲሆን አትሌት አሰለፈች መርጊያ እና አትሌት ሰንበሬ ተፈሪም በውድድሩ ላይ ተገኝተው ለተወዳዳሪዎች ሽልማት አበርክተዋል፡፡

መነሻ እና መድሻውን አትላስ መብራት ላይ ያደረገው የዛሬው ሩጫ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ከግምት ውስጥ ያስገቡ ዝግጅቶችን ያደረገ ሲሆን፡ ተሳታፊዎች ማስክ በማደረግ፤ ሳኒተይዘር በመጠቀምና እርቀታቸውን በመጠበቅ ላደረጉት ትብብር አዘጋጆች ምስጋናቸውን ቸረዋል፡፡

በ2013 ሶፊ ማልት ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ ሩጫ በአትሌቶች ውድድር ፋንታዬ በላይነህ ከአዲዳስ ልማት ግሩም በ15፡19፡00 አንደኛ፤ አትሌት መድህን ገብረ ስላሴ ከንግድ ባንክ በ15፡25፡00 ሁለተኛ እና አትሌት ፈታው ዘርዓይ ከንግድ ባንክ በ15፡33፡00 ሶስተኛ ሆነው አጠናቀዋል፡፡ አሸናፊዋ አትሌት ፋንታዬ በላይህም የ50 ሺ ብር ተሸላሚ ሆናለች፡፡

በሌሎች የውድድር ዘርፎች ከወጣት ተፅእኖ ፈጣሪ ቡድን ሊዲያ ወንዶሰን አንደኛ፤ ዮርዳኖስ አባይነህ ሁለተኛ፤ ያይኔአበባ አሰግድ ሶስተኛ ጥሩወርቅ አሰፋ ሆነው ውድድሩን ሲያጠናቅቁ፡፡ በሶፊ ማልት ፊትነስ ውድድር ደግሞ አንደኛ ራሄል ጌታቸው፤ ሁለተኛ እታለም ገብሬ እንዱሁም ሶስተኛ ወጥተዋል፡፡

More To Explore

10KM

የ2015 ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ ዘመቻ የታቀደለትን ገቢ አሰባስቦ ለሶስት በጎ አድራጎት ድርጅቶች አስረከበ፡፡

በዘመቻው ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በተለያዩ መንገዶች ተሰብስቧል፡፡ ታህሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም.፡- ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ቢሮ ጋር በመተባበር የተለያዩ