በውድድሩ ማማሟቂያ የተሳተፈው ኃይሌ ገብረስላሴ ለተሳተፊዎች መደበኛ የሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አስፈላጊነት ለተሳተፊዎች ተናግሯል ፡፡ “ያልሮጥኩ ቀን ቀን ምግብ እንዳልበላሁ ነው የምቆጥረው” የሚለው ኃይሌ ጤናማ ለመሆን ከፈለግን ሩጫ የአኗኗራችን አካል ወይም ባህል መሆን እንዴት እንደሚያስፈልግ አስረድቷል ፡፡
የ 5 ኪ.ሜ ሩጫ በወንዶች ምድብ በአብደራዛቅ አለዊ ለሁለተኛ ጊዜበ19:41:99 በሆነ ሰዓት ሲያሽንፍ በሴቶች ውድድር ደግሞ ራያ አማን በ 26:01:25 በሆነ ሰዓት አሸናፊ ሆናለች ፡፡
በሰላሳ የመገናኛ ብዙሃንተወካዮች መካከል በተደረገው ውድድር ታደሰ አቢዩከብስራት ሬዲዮ እና ሃይማኖት ወርቅነህ ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ አሸናፊዎቹ ሆነዋል ፡፡