የጃኖዎቹ – ሔዋንና ሃሌሉያ

Share This Post

Share on facebook
Share on linkedin
Share on twitter
Share on email

ሔዋን ትሮጣለች፡፡ ድምጻዊት እንደመሆንዋ በተለይ የመንገድ ሩጫን እንደ ጥሩ ትንፋሽ ማስተካከያ ትጠቀምበታለች፡፡ ሙዚቃ እየሰማች እስከ 6ኪሎ ሜትር ትሮጣለች፡፡ አካላዊ ብርታትዋን እና ጥንካሬዋን ለመጠበቅ ደግሞ ወደ ጂም ትሄዳለች፡፡ “በይበልጥ ግን መንገድ ላይ የምሮጠው ይበልጣል” ትላለች፡፡ ጃኖ ከመጀመሯ ቀደም ባለው ጊዜ እንዲያውም ክብደቷን ለመቆጣጠር እና በሌሎችም ምክንያቶች በሳምንት ሰባቱን ቀናት የምትሰራበት ጊዜ ነበር፡፡

“ስቴጅ ላይ ትንፋሽ ያስፈልጋል፡፡ እሰከ ሶስት ሰዓት ስቴጅ ላይ እንቆያለን፡፡ ባንዱን ካየኸው የራሳችንን ዘፈን ብቻ ዘፍነን አንወርድም፡፡ እንዘፍናለን. . .  ደሞ አንዱ ሲዘፍን ሌላው ሀርመኒ ይሰራል፡፡ ባክግራውንድ ተቀባይ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ትንፋሽህ ጥሩ ሲሆን ረጅም ሰዓት ትሰራለህ፡፡ በተጨማሪም ብርታቱ ይኖርሀል፡፡ ስፖርት የምትሰራ ከሆነ ሬዚስት ታደጋለህ ወይም አይደክምህም፡፡ የሚገርምህ ነገር. . . አንዳንድ ጊዜ ሾዉ አልቆም ቀጥለን መስራት የሚያስችለን ጉልበት ይኖረናል፡፡ ጥቂት ጊዜ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ሳንሰራ ስንቀር ግን ውጤቱ ወዲያው ይታያል፡፡ ድካምና ቶሎ ቶሎ መተንፈስ ስትጀምር ታውቀዋለህ” ትላለች ሔዋን፡፡

ሌላኛዋ የባንዱ አቀንቃኝ ሃሌሉያ “በቤቴ የምሰራው ስፖርት ያመዝናል” ትላለች፡፡ “ገመድ መዝለል፣ ዮጋ እና ስትሬች ማድረግ እና የመሳሰሉ አነስ ያሉትን አዘወትራለሁ፡፡ ስቴጅ ላይ በጣም ይጠቅመናል፡፡ አስተውለኸው ከሆነ የኛ ሙዚቃዎች እንቅስቃሴ ይፈልጋሉ፡፡ ስፖርት ካለሰራህ ከባድ ይሆንብሃል፡፡ እኔ ቤት ውስጥ ብዙ ውሃ (ከ2-4 ሊትር) እየጠጣሁ በቤቴ እሰራለሁ፡፡ ሄዊ (ሄዋን) ጎበዝ ናት. . . ትሮጣለች፡፡ (በሴቶቹ ሩጫ) እሷን እያባረርኳት ነው በቡድን ሶስተኛ የወጣነውና ዋንጫውን የወሰድነው፡፡” (. . . ሁለቱም ይስቃሉ)  

ሔዋን በሩጫው የተለየ ካታጎሪ እንደነበረው እንዳላወቁ ትናገራለች፡፡ ሃሌሉያም “አዎን. . . አንቺ ትብሽ አንቺ ትብሽ እየተባባልን ነበር ተያይዘን የመጣነው፡፡ ከህዝቡ ጋር ፈን እያደረግን ነበር የመጣነው፡፡ ሰልፊ እየተነሳን፤  ስለስራም እያወራን፤ ከአዲሱ አልበማችን (ለራስህ ነው) የያዝናቸውን ሲዲዎች ለዲጄዎቹ እና ለህዝቡ እየሰጠን ነው የሮጥነው፡፡ መጨረሻ አካባቢ ስንደርስ ውድድር ነውኮ ስንባል ሄዊ አፈትላካ ሮጠች፡፡”

ለሔዋንና ሀሌሉያ ታላቁ ሩጫ የመጀመሪያቸው ነው፡፡ “የሚተላለፈው ሀሳብ ደስ ይላል፡፡ የነበረው ስሜት፣ ስፖርቱ፣ ሙዚቃው ባጠቃላይ የነበረው ቫይብ ደስ ይላል፡፡”

አሁን ከሁለቱ ድምጻዊያን ጋር አጫጭር ጥያቄና መልስ ይኖረናል፡፡

ሔዋን

ቅጽል ስምሽ?

የቅርብ የምላቸው ቤተሰቦቼና ጓደኞቼ ፊፊ ይሉኛል፡፡

አብልጠሸ የምትወጂው ስፖርት?

ሩጫ እወዳለሁ፡፡ ተወዳዳሪ/አትሌት/ ብሆን ደስ ይለኝ ነበር፡፡  

መከታተል/መመልከት የምትወጂው ስፖርት?

እኔ. . . (ሃሌሉያ እየሳቀች ጣልቃ ትገባለች)፡፡ ቱር ስናደርግ እኔ እና እሷ አብረን ነው ሩም የምንይዘው፡፡ እና ገና ስንገባ በቀጥታ ሄዳ ኳስ ከፍታ ታያለች፡፡ እኔ ኧረ ሄዊ በናትሽ እያልኩ እለምናታለሁ (ይስቃሉ)፡፡ እኔ የማን ይሁን የምን ይሁን አላውቅም፡፡ ግን በቃ በስሜት ሆና ነው የምታየው…ታስቅሃለች፡፡ ደሞ ልታብራራልኝ ያምራታል. . . እኔ አይገባኝም፡፡ (ሔዋን ተመልሳ) ሁሉንም አያለሁ ግን ማንቸስተር ዩናይትድ ደስ ይለኛል፡፡ ቤታችን ውስጥ ወንዶች ይበዙ ነበር፡፡ ወንድሞቼና አጎቶቼ ኢንፊዩሌንስ ያረጉኝ ይመስለኛል፡፡

ከልጅነቴ በለመድኩት ኖሮ የምትይው ስፖርት?

ውሹ ነው፡፡ እንዲያውም ሃይስኩል እያለሁ ገብቼ ነበር፡፡ ቀደም ብዬ ብጀምረው ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ስጀምረው ሰዎች ምንድነው ይሄ መራገጥ ምናምን እንባል ነበር፡፡ ነገር ግን ስነ ምግባር የምትማርበትና ሌላም ብዙ አርት ነበረው ውስጡ፡፡ በኋላ ዪኒቨርሲቲ ምናምን ሲመጣ ቀረ፡፡

የጂም ውስጥ ተመራጭ የስፖርት ማሽን/መሳሪያ?

ትሪድሚል /መሮጫ ማሽን/ እና ጆግ ማድረጊያው ማሽን /Elliptical/፡፡ የመሮጫው ማሽን ግን ራሱ የሚጠራኝ ነው የሚመስለኝ (ሳቅ)፡፡

ሃሌሉያን ብትገጥሚያት በእርግጠኛነት የምታሸንፊያት ስፖርት?

ሩጫ ይመስለኛል፡፡

በሙዚቃው አለም የምትደነቂባቸው?

                                     ከሀገር ውስጥ፡- አስቴር አወቀ እና እጅጋየሁ ሽባባው /ጂጂ/

                                     ከሀገር ውጪ፡- ቢዮንሴ

ሃሌሉያ

ቅጽል ስምሽ?

አሁን አሁን እንጂ ሃሌሉያ የሚለው ስም የተለመደው ቤት ውስጥና ሌሎችም ብዙ ሰዎች የሚያውቁኝ “ሉቺያ” በሚል ስሜ ነው፡፡ አባቴ ነው ያወጣልኝ፡፡ መብራት ማለት ነው፡፡

አብልጠሽ  የምትወጂው ስፖርት?

ያው ገመድ መዝለል ነዋ! (ሳቅ)

መከታተል/መመልከት የምትወጂው ስፖርት?

ብዙም ስለኳስ አላውቅም፡፡ ሌላም ውድድር ብዙም አላይም

ከልጅነቴ በለመድኩት ኖሮ የምትይው ስፖርት?

ስፖርት አይባልም ከሆነ አላውቅም፡፡ እኛ ሀገር ያለ አይመስለኝም፡፡ ቢኖርና ብማረው የምወደው ግን ‘ባሌት’ ዳንስ ነው፡፡

የጂም ውስጥ ተመራጭ የስፖርት ማሽን/መሳሪያ?

የሩጫው ማሽን

ሔዋንን ብትገጥሚያት በእርግጠኛነት የምታሸንፊያት ስፖርት?

በዮጋ ምናምን. . . በቃ እበላታለሁ (ረጅም ሳቅ)፡፡

በሙዚቃው አለም የምትደነቂባቸው?

                                     ከሀገር ውስጥ፡- አስናቀች ወርቁ

                                     ከሀገር ውጪ፡- ማይክል ጃክሰን፡፡ 

More To Explore

10KM

የ2015 ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ ዘመቻ የታቀደለትን ገቢ አሰባስቦ ለሶስት በጎ አድራጎት ድርጅቶች አስረከበ፡፡

በዘመቻው ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በተለያዩ መንገዶች ተሰብስቧል፡፡ ታህሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም.፡- ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ቢሮ ጋር በመተባበር የተለያዩ