የአይኤፍኤች ኢንጂነሪንግ 20ኛ አመት የምስረታ በአል ከሳርቤት እስከ ጎተራ በዱላ ቅብብል ውድድር ሊያከብር ነው

Share This Post

Share on facebook
Share on linkedin
Share on twitter
Share on email

አይኤፍኤች ኢንጂነሪንግ (በቀድሞ ስሙ ‘ሲአርቢሲ አዲስ ኢንጂነሪንግ’ ተብሎ ይንቀሳቀስ የነበረው) እሁድ ሐምሌ 10 ቀን 2014 የሚካሄደውን የ2014 የአይኤፍኤች የዱላ ቅብብል ስፖንሰር በማድረግበኢትዮጵያ የ20 ዓመታት ስራውን ያከብራል።

ውድድሩ የሚካሄደው በአይኤፍኤች በተጠናቀቀው ከሳርቤት ፑሽኪን አደባባይ ወደጎተራ ማሳለጫ መንገድ ከአዲስ አበባ በደቡብ በኩል ባለው አዲስ መንገድ ላይ ነው።

አይኤፍኤች ኢንጂነሪንግ እነዚህን የዱላ ቅብብሎሽ ለመጀመሪያ ጊዜ ስፖንሰር ያደረገው በ 1997 ዓ.ም ከቃሊታ እስከ መገናኛ ባለው የአዲስ አበባ ቀለበት መንገድ ምስራቃዊ ዝርጋታ መጠናቀቁን ምክንያት በማድረግ ነበር። በ1999 ለሦስተኛ ጊዜ በድጋሚ ከተካሄደው የዱላ ቅብብል ውድድር በኋላ ኩባንያው ከአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን (አአአክራ) ጋር በመተባበር ዝግጅቱን በከተማዋ ወደሚገኙ ሌሎች ቦታዎች ተዘዋውሮ ባስገነባቸው ሌሎች አዳዲስ መንገዶች ላይ አክብርዋል።

በቅርብ ጊዜ የተካሄደው፣ 16 ኛው ተከታታይ አመታዊ የዱላ ቅብብል ውድድር፣ የተካሄደው ከሦስት ዓመታት በፊት በ 2011 የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከመከሰቱ በፊት ነበር።

ባለፉት ሃያ ዓመታት አይኤፍኤች ኢንጂነሪንግ የመንገድና ድልድይ ግንባታ ፕሮጀክቶቹን ባከናወነበት ፍጥነት መልካም ስም አትርፏል። ከፕሮጀክቶቹ መካከል የአዲስ አበባ ቀለበት መንገድ፣ የኢትዮ-ቻይና ወዳጅነት መንገድ በወሎ ሰፈር፣ የቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ማኮብኮቢያ ማሻሻያና ማስፋፊያ ፕሮጀክት፣ ከመገናኛ እስከ አያት መንገድ፣ ከመገናኛ እስከ ጦርኃይሎች መንገድ፣ ከመስቀል አደባባይ እስከ ቃሊቲ መንገድ ድረስ ያሉ ፕሮጀክቶች ይገኙበታል።

የአይኤፍኤች ኢንጂነሪንግ ዋናስራ አስኪያጅ አቶ ዢያኦ ዚቺያንግ እንዳሉት “ባለፉት ሃያ አመታት በከተማዋ ኢኮኖሚ ልማት ውስጥ በቅርብ ተሳትፈናል። አላማችን የኢትዮጵያ ዋና ከተማን የተሻለ የመኖሪያ ቦታ ለማድረግ እና በመላ ከተማዋ የትራንስፖርት ግንኙነቶችን ለማሻሻል ነው”።

በድጋሚ በዚህ አመት በሚካሄደው ውድድር ላይ 150 የሚሆኑ ቡድኖች በቡድን 8 ተሳታፊዎችን አቅፈው የተለያዩ የንግድ እና ሌሎች ድርጅቶችን ወክለው ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

More To Explore

10KM

የ2015 ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ ዘመቻ የታቀደለትን ገቢ አሰባስቦ ለሶስት በጎ አድራጎት ድርጅቶች አስረከበ፡፡

በዘመቻው ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በተለያዩ መንገዶች ተሰብስቧል፡፡ ታህሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም.፡- ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ቢሮ ጋር በመተባበር የተለያዩ