የአትሌቶች 10ኪ.ሜ. ውድድር በግል ለሚሳተፉ 94 ያህል ተወዳዳሪዎች የማጣሪያ ውድድር በቅዳሜ መስከረም 29 ቀን አካሄደ፡፡

Share This Post

Share on facebook
Share on linkedin
Share on twitter
Share on email

መስከረም 29 ቀን 2014 ዓ.ም.

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በ2014 ቶታልኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለሚካሄደው የአትሌቶች 10ኪ.ሜ. ውድድር በግል ለሚሳተፉ 94 ያህል ተወዳዳሪዎች የማጣሪያ ውድድር በቅዳሜ መስከረም 29 ቀን አካሄደ፡፡

ከባለፉት ሁለት አመታት ጀምሮ መደረግ የጀመረው የግል ተወዳዳሪ አትሌቶች የማጣሪያ ውድድር ዘንድሮ ለ3ተኛ ጊዜ ተካሂዷል፡፡ በዚህም ማጣሪያ ላይ ከአንድ እስከ ሶስት ለወጡ ተወዳዳሪዎች የማበረታቻ ገንዘብ ሽልማት ከቶታል ኢነርጂስ ዋና ስራ አስኪያጅ- አን ሶፊ ማይል አበርክተውላቸዋል፡፡

በውድድሩ ተሳትፈው አሸናፊ የሆኑት አትሌቶች በወንዶች ብርሃኑ ታሌ በ15፡35፡50 ደቂቃ አሸናፊ ሲሆን ሚሊዮን ኡርጌ በ16፡14፡60 ደቂቃ እና አዲሱ ስዩም በ16፡20፡40 ደቂቃ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ወጥተዋል፡፡ በሴቶች ውድድር ደግሞ ምስራቅ በድሉ በ18፡39፡40 ደቂቃ አንደኛ ጫልቱ ተፈሪ በ20፡19፡80 ሁለተኛ ሸዋዩ ስንሻው ደግሞ በ20፡39፡70 ደቂቃ ሶስተኛ ወጥተዋል፡፡

የ2014 ቶታልኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለመካሄድ 5 ሳምንታት ብቻ የሚቀሩት ሲሆን የዚህም ውድድር አጋር ድርጅቶች ቶታልኢነርጂስ የስያሜ ስፖንሰር፤ ዩኒሴፍ – መፀዳዳት በሽንት ቤት በሚል የመልዕክት አጋር፤ ሶፊ ማልት፤ አሞሌ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የክብር ስፖንሰሮች ሲሆኑ በተጨማሪም ቱሪዝም ኢትዮጵያ፤ ሃያት ሬጀንሲ ሆቴል፤ አርኪ ውሃ እና ሳስ ፋርማሲስ እና ኢንዶሚ የዘውትር አጋሮች በዘንድሮውም ውድድር ላይ አጋርነታቸውን ቀጥለዋል፡፡

More To Explore

10KM

የ2015 ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ ዘመቻ የታቀደለትን ገቢ አሰባስቦ ለሶስት በጎ አድራጎት ድርጅቶች አስረከበ፡፡

በዘመቻው ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በተለያዩ መንገዶች ተሰብስቧል፡፡ ታህሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም.፡- ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ቢሮ ጋር በመተባበር የተለያዩ