የቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ ለ18ተኛ ጊዜ ‘የኢትዮጵያ ሴቶችን ስኬት እናክብር’ በሚል መርህ ይካሄዳል

Share This Post

Share on facebook
Share on linkedin
Share on twitter
Share on email

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሃ/የ/የግል ማህበር ላለፉት 17 አመታት ሴቶችን ብቻ የሚያሳትፈውን የቅድሚያ ለሴቶች ሩጫ ያለ ማቋረጥ ሲያካሄድ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ የኢትዮጵያ ሴቶችን ስኬት ከተለያዩ የሩጫ መልዕክት ጋር እያያያዘ ሲያከብር የመጣው ይህ ሩጫ ዘንድሮ ለ18ተኛ ጊዜ ይከበራል፡፡

ዘንድሮ ሶፊ ማልት የስያሜ ስፖንሰር ነው፡፡ ውድድሩም የ2013 ሶፊ ማልት ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ ሩጫ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ከዚህ ቀደም ሩጫው በሚካሄድበት አትላስ ሆቴል አካባቢ መነሻ እና መድረሻውን አድርጎ እሁድ መጋቢት 19 ቀን 2013 ዓ.ም. ይካሄዳል፡፡ 18 አመት የሚሞላው የዘንድሮ የቅድሚያ ለሴቶች ሩጫ በኮቪድ 19 ወረርሺኝ ምክንያት ሊያሳትፍ ካቀደው 15000 ተሳታፊ በመቀነስ 13 በመቶ የሚሆነውን 2000 ሴት የጤና ሯጮች የሚያወዳድር ሲሆን፤ ከ2000 ተሳታፊዎችም በተጨማሪ 150 አትሌቶች ተሳታፊ ከተወሰኑ የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት ተጋባዥ የሚሆኑበት ውድድር ይሆናል፡፡ በዚህ ውድድር ላይ ኮቪድ 19ኝን ከግምት ውስጥ በማስገባት ልዩ ጥንቃቄና ዝግጅት ተደርጓል፤ ለተሳታፊዎች መነሻና መድረሻ ላይ የሚያደርጉት የፊት ጭምብል፤ የሰውነት ሙቀት ልኬት እና ሳኒታይዘር የሚደረግ ሲሆን ውድድሩንም በተቻለ መጠን አላካዊ ርቀትን የጠበቀ እንዲሆን በሁለት የተለያየ ማዕበል መነሻ እንዲኖር ቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል፡፡

አሰለፈች መርጊያ የእለቱ ጋዜጣዊ መግለጫን በሆቴልዋ ያስተናገደች ሲሆን የቅድሚያ ለሴቶች ሩጫ የ1999 ዓ.ም. እና 2001 ዓ.ም. አሸናፊ ስትሆን የሴቶቹ ሩጫ ድሏ አሁን ለደረሰችበት ስኬት የጎላ አስተዋፅኦ እንዳለው ትገልፃለች፡፡

የዚህን ውድድር የመክፈቻ እና የምዝገባ ቀን ማሳወቂያ ፕሮግራም በዛሬው እለት በአትሌት አሰለፈች መርጋ ሆቴል የተካሄደ ሲሆን በዝግጅቱ ላይ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የስያሜ ስፖንሰር የሆነው ሶፊ ማልት፤ የምዝገባ አጋር የሆነው እናት ባንክ፤ አይሪሽ ኤድ፤ ሃያት ሬጀንሲ፤ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት፤ አርኪ ውሃ እና ዋሽንግተን ህክምና ማዕከል ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

የ2013 ሶፊ ማልት ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ ምዝገባ በሶስት የእናት ባንክ ቅርንጫፎች በካሳንቺስ (እቴጌ ጣይቱ ቅርንጫፍ)፤ ደራርቱ ቱሉ (ሜክሲኮ ቅርንጫፍ) እና አበበች ጎበና (መገናኛ አካባቢ) እና በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ቢሮ በተጨማሪም በእናት ባንክ የኦንላን ምዝገባ በመጠቀም መመዝገብ እንደሚችሉ ታውቋል፡፡ ምዝገባ ጥር 23 ቀን ይጀመራል፡፡

ተሳታፊዎች ለውድድሩ ቀን በተሻለ የአካል ብቃት ላይ እንዲገኙ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ማዘውተርን ለማበረታታት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የአራት ተከታታይ ሳምንታት የልምምድ ፕሮግራም አዘጋጅቷል፡፡ በዚህ ሳምንታዊ የልምምድ ፕሮግራም ቀድመው የተመዘገቡ 50 ሴቶች የሚሳተፉበት ሲሆን ልምምዱ በአሰልጣኝ የታገዘ እና የዋናው ውድድር የመሮጫ መንገድን ጨምሮ በተለያዩ የመሮጫ ቦታዎች በነፃ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

More To Explore

10KM

የ2015 ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ ዘመቻ የታቀደለትን ገቢ አሰባስቦ ለሶስት በጎ አድራጎት ድርጅቶች አስረከበ፡፡

በዘመቻው ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በተለያዩ መንገዶች ተሰብስቧል፡፡ ታህሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም.፡- ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ቢሮ ጋር በመተባበር የተለያዩ