የሶፊ ማልት ወርቅ ሜዳልያ ያልሙ የሩጫ ልምምድ ፕሮግራም ዛሬ ተጀመረ::

Share This Post

Share on facebook
Share on linkedin
Share on twitter
Share on email

ሰማንያ ተሳታፊዎች የተገኙበት የ8 ሳምንት የልምምድ ፕሮግራም የሆነው ከሶፊ ማልት ጋር ለወርቅ ይነሱ ፕሮግራም ዛሬ ጠዋት በያያ ቪሌጅ ተካሄደ፡፡ ተሳታፊዎች በሩጫ አለማማጅ አትሌቶች ታግዘው እንደአቅማቸው ከ4ኪ.ሜ እስከ 7ኪ.ሜ ሮጠዋል፡፡ የዚህ ፕሮግራም ዋና አላማ ተሳታፊዎች ሩጫን ለመለማመድ ከሚፈልጉ ሌሎች ተሳታፊዎች ጋር በመሆን የሩጫ ባህልን እንዲያዳብሩና መጀመሪያ ለማጠናቀቅ ያለሙትን ርቀት (20ኪ.ሜ፤ 30ኪ.ሜ ወይም 42ኪ.ሜ) በተያዘው ጊዜ ማጠናቀቅ እንዲችሉ ለመርዳት ነው፡፡

ከተሳታፊዎች መካከል ሶስት እህትማማቾች ሆነው የተሳታፉት የሸዋ እንዳለችው – ላለፉት 2 አመታት ምንም አይነት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እኔም ሆንኩ እህቶቼ አላደረግንም፡፡ እኔ በቅርቡ የልጅ እናት ሆኛለሁ፡፡ የዛሬው ልምምድ ትንሽ ከብዶኝ ነበር ግን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማድረግ እንድበረታታ አድርጎኛል፡፡ ከእህቶቼም ጋር ቢያንስ በቋሚነት ሰፈር ውስጥ በእግራችን ለመራመድ ተስማምተናል፡፡ የእንጦጦ ፓርክ ሩጫንም ለመቀላቀል አቅደናል፡፡ ዛሬ ካየነው ፕሮግራም የሚቀጥለውን የልምምድ ፕሮግራም ለመሳተፍ ጓጉተናል፡፡

ይህ የልምምድ ፕሮግራም ለጤና ጠቃሚ በሆኑ ንጥረ ነገሮች የዳበረው ሶፊ ማልት በአጋርነት አብሮ የሚያዘጋጀው ፕሮግራም ነው፡፡ ያያ ቪሌጅም የዚህ ልምምድ አጋር ነው፡፡ በልምምድ መክፈቻ ፕሮግራም ላይ አትሌት ሃይሌ ገ/ስላሴ ተገኝቶ ተሳታፊችን አበረታቷል፡፡

ቀጣዩ የልምምድ ፕሮግራም እሁድ ሰኔ 5 ቀን 2013 በያያ ቪሌጅ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

More To Explore

10KM

የ2015 ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ ዘመቻ የታቀደለትን ገቢ አሰባስቦ ለሶስት በጎ አድራጎት ድርጅቶች አስረከበ፡፡

በዘመቻው ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በተለያዩ መንገዶች ተሰብስቧል፡፡ ታህሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም.፡- ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ቢሮ ጋር በመተባበር የተለያዩ