ዘንድሮ ለ19ኛ ጊዜ የሚካሄደው የቅድሚያ ለሴቶች ውድድር በ10ሺ ተሳታፊዎች ዛሬ በትላስ አካባቢ ተደርጓል፡፡

Share This Post

Share on facebook
Share on linkedin
Share on twitter
Share on email

መጋቢት 4 ቀን 2014 ዓ.ም. ፡- የሴቶች ብቻ የሆነው እና ዘንድሮ ለ19ኛ ጊዜ የሚካሄደው የቅድሚያ ለሴቶች ውድድር በ10ሺ ተሳታፊዎች ዛሬ በትላስ አካባቢ ተደርጓል፡፡

የዛሬውን ውድድር 7500 አካባቢ ተሳታፊዎች የተካፈሉበት ሲሆን ውድድሩ አትሌቶችን አምባሳደሮችን እና የኢትዮጵያ ተምሳሌት ሴቶችን አካቷል፡፡

በአትሌቶች ውድድር የ22 አመትዋ ፈንታዬ በላይነህ አንደኛ በመውጣት የ50ሺ ብር ተሸላሚ ስትሆን፤ በትራክ ላይ ሩጫ የ14 ደቂቃ 44 ሰከንድ በሄንገሎ፤ ሆላንድ በመሮጥ ጥሩ ሰኣት አስመዝግባለች፡፡

በቅድሚያ ለሴቶች ውድድር ላይም ፋንታዬ ስታሸንፍ ይህ ለሁለተኛ ጊዜዋ ነው፡፡ ፋንታዬ የዘንድሮውን ውድድር በ15 ደቂቃ ከ30 ሰከንድ አጠናቃለች፡፡ ፋንታዬን ተከትለው ሁለተኛ እና ሶስተኛ በመሆን ያጠናቀቁት መቅደስ አበራ (15፡33) እና ቃልኪዳን ፋንቴ (15፡37) ናቸው፡፡ ሶስቱም አትሌቶች የአዲዳስ ልማት ግሩፕ አባላት ናቸው፡፡

የኢፊድሪ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በውድድሩ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ውድድሩንም አስጀምረዋል፡፡በመክፈቻው ላይም “በሴቶች እኩልነትና መብት ማስከበር ቢሠራም ብዙ ይጠበቃል ሀገርን ለማሳደግ: ሴቶችንየሚገባቸው ቦታለማድረስ… ብዙ ሩጫዎች ይቀሩናል: ጊዜየለንም” ብለዋል።

በውድድሩ ላይ አትሌት ሃይሌ ገ/ስላሴ እና የውድድሩ አምባሳደር የሆነችው አትሌት መሰረት ደፋር በክብር እንግድነት ተገኝተዋል፡፡

ውድድሩን ለማጠናቀቅ የመጀመሪያዋ የውጭ ሃገር ተሳታፊ የሆነችው ሊያ ኢማን ስትሆን ውድድሩን በ23 ደቂቃ አጠናቃለች፡፡ የመጀመሪያ ሆና ያጠናቀቀችው ሴት አምባሳደር የዴንማርኳ ኪራ ስሚዝ ናት፡፡

More To Explore

10KM

የ2015 ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ ዘመቻ የታቀደለትን ገቢ አሰባስቦ ለሶስት በጎ አድራጎት ድርጅቶች አስረከበ፡፡

በዘመቻው ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በተለያዩ መንገዶች ተሰብስቧል፡፡ ታህሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም.፡- ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ቢሮ ጋር በመተባበር የተለያዩ