ጋዜጣዊ መግለጫ
ሚያዚያ 29 ቀን 2013 ዓ.ም.
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሃ.የ.የግል ማህበር ለወትሮ ከሚያደርጋቸው ህዝባዊ ሩጫዎች በተጨማሪ ለየት ባለ መልኩ የተሳታፊ ቁጥራቸው አነስ ያለ እና በተደጋጋሚ የሚከናወኑ ውድድሮችን ማድረግ መጀመሩ ይታወቃል፡፡
ከዚህም ጋር በተያያዘ ከሶፊ ማልት ጋር በመተባበር በአይነቱ አዲስ የሆነ ለ4 እሁዶች የሚካሄድ ለሁሉም የቤተሰብ አባላት የሚሆን የልምምድ ፕሮግራም አዘጋጅቷል፡፡ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ – ሩጫን ለሁሉም የኑሮ ዘይቤ ማድረግ የሚል ራእይ ላይ መስራት መጀመሩ የዚህ አይነት ዝግጅቶችን አዘውትሮ ለማካሄድ እንዲተጋ አድርጎታል፡፡
የዚህ ለወርቅ ይሩጡ ልምምድ ለ7 ተከታታይ ሳምንታት የሚካሄድ ሲሆን ከ7ቱ ሳምንታት ውስጥ ለ4 እሁዶች በያያ ቪሌጅ የልምምድ ፕሮግራም የሚካሄድ ይሆናል፡፡ በአራት እሁዶች (ማለትም ግንቦት 22 ፣ ሰኔ 6 ፣ ሰኔ 20 እና ሐምሌ 4 ቀን 2013 ዓ.ም.) ተሳታፊዎች በመረጡት የኪ.ሜ ርቀት መሰረት በአሯሯጭ የታገዘ ልምምድ ያደርጋሉ ፡፡ ተሳታፊዎች በያሉበት ቦታ ሆነው መመዝገብ እንዲችሉ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የኦን ላይን መዝገቢያ ያዘጋጀ ሲሆን ይህንን ሊንክ https://ethiopianrun.org/en/races/run-for-gold በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ፡፡
በዚህ የልምምድ ፕሮግራም ላይ ተሳታፊዎች አቅማቸው በሚፈቅደው መጠን መሳተፍ እንዲችሉ በማሰብ የተለያዩ ርቀት ያላቸው የልምምድ ፕሮግራሞች ተዘጋጅተዋል፡፡ 42 ኪ.ሜ. ወይም ማራቶን የመሮጥ አቅም ያላቸው በ7 ሳምንታት በተከፋፈለ መልኩ የልምምዱ ተሳታፊዎች ይሆናሉ፡፡ ልምምዱ ጀማሪ ሯጮችንም ታሳቢ በማድረግ የ30ኪ.ሜ. እና የ20ኪ.ሜ. ልምምዶችን እንዲሁም ለህፃናት የሚሆኑ ዝግጅቶችን ያካትታል፡፡
በኢትዮጵያ የጥቁር ማልት መጠጥ በማቅረብ የመጀመሪያ የሆነው እና 100% ተፈጥሮአዊ ውህድ የሆነው ሶፊ ማልት የዚህ ልምምድ ፕሮግራም ብቸኛ አጋር ድርጅት ሲሆን ከቫይታሚን፤ ሚኒራል እና ካልሺየም የበለፀገ መጠጥ መሆኑ ተመራጭ ያደርገዋል፡፡ ጤናማ አኗኗርን በማህበረሰቡ ውስጥ ልምድ እንዲሆን በማድረግ የላቀ አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ ያለው ሶፊ ማልት ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር ላለፉት አመታት አብሮ በመስራት ይታወቃል፡፡
ለበለጠ መረጃ ፡- hilina@ethiopianrun.org ወይም በስልክ ቁጥር 0911601710 ይጠይቁ፡፡