የእንጦጦ ፓርክ ፕሬደተር ሩጫ በዋነኛነት አላማው ተሳታፊዎች የጤናማ አኗኗር ዘይቤን እንዲያዘወትሩ ከራሳቸው ጋር በየወሩ ያላቸውን የፍጥነትና ብቃት ልዩነት እየለኩ ጤንነታቸውን እንዲጠብቁ ያበረታታል፡፡ በተጨማሪም ተሳታፊዎች የዲጂታል የሩጫ ውጤት ማግኛ መንገድን በቀላሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡
የእንጦጦ ፓርክ ለጤና እና ለስፖርት ተስማሚ የሆነ በተጨማሪም የሩጫ ቦታ መሆኑን ለተሳታፊዎች እና ለተለያዩ የውጪ እና ሃገር ውስጥ ቱሪስቶች እየመጡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማዘውተሪያ እንዲያደርጉት የተዘጋጀ እንደመሆኑ መጠን ይህ ውድድር እንደ ማሳያነት የሚሆን ወርሃዊ ዝግጅት ነው፡፡
አብዛኛዎቹ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድሮች እሁድ ቀን የሚካሄዱ ቢሆንም ወርሃዊው የእንጦጦ ፓርክ ፕሬደተር ሩጫ በወር አንዴ በመካሄዱ እና ቅዳሜ ጠዋት በመሆኑ ውድድሩን ከሌሎች ውድድሮች ለየት ያደርገዋል፡፡ ይህ ውድድር በየወሩ ኦንላይን በሚደረግ አመዘጋገብ 200 ተሳታፊዎችን በነፃ ያስተናግዳል፡፡ የእንጦጦ ፓርክ ፕሬደተር 5ኪ.ሜ. ሩጫ በየወሩ ከጠዋቱ 2፡30 የሚደረግ ይሆናል፡፡
ስለ የፕሬደተር አሸናፊ ፡-
የዚህንም መጠጥ ስያሜ ለሩጫ ፈታኝ በሆነው በእንጦጦ ፓርክ ውስጥ ሮጠው በአሸናፊነት የሚያጠናቅቁ ተሳተፊዎች አንደኛ ፕሬደተር የሚል ስያሜ ይሰጣቸዋል፡፡ በአመት ውስጥ 3 ጊዜ የሚያሸንፉ ተሳታፊዎች ደግሞ የፕሬደተር ልዩ ዋንጫ የሚበረከትላቸው ይሆናል፡፡ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በየአመቱ የሚታደስ የአባልነት ፕሮግራም መጀመሩ የሚታወቅ ሲሆን ተሳታፊዎች አባል ለመሆን የበለጠ መረጃ በውድድሩ ቀን ማብራሪያ ማግኘት የሚቻል መሆኑ ታውቋል፡፡