ሰኔ 1፣ 2014 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ፣ በወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ እና በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መካከል በዛሬው እለት በከተማዋ እንደ ስፖርት ያሉ ቱሪስቶች የመሳብ አቅም ያላቸውን እንቅስቃሴዎች በጋራ በመተባበር፣ በማልማትና በማበልፅግ የስፖርት ቱሪዝምን እንዲስፋፋ ለመስራት የሶስትዮሽ ስምምነት ተፈራርመዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ ክብርት ዶክተር ሂሩት ካሳው፣ የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ እና የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መስራች ሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ በተገኙበት ስምምነቱ ተካሂዷል።