ግንቦት 09 ቀን 2014 ዓ.ም. – ለ21 አመታት ያለመቋረጥ የተካሄደው እና ለበርካታ አትሌቶች የመፎካከሪያ መድረክ በመፍጠር ተቀዳሚ ቦታን የያዘው አመታዊው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል 10ኪሜ ውድድር በየወሩ የሚወጣው ራነርስ ወርልድ መፅሄት በዚህ ወር ዝርዝሩ ላይ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በአለም ላይ ካሉ ታዋቂ የ10ኪሜ ውድድሮች ውስጥ በቀዳሚነት ተጠቃሽ ነው ሲል አስፍሮታል፡፡ ራነርስ ወርልድ የተለያዩ የሩጫ ዜናዎችን፤ የስልጠና ጠቃሚ መልእልቶችን፤ አነቃቂ ታሪኮችንና ከሩጫ ጋር ተያያዥ የሆኑ መረጃዎችን በመስጠት በአለም ላይ በማሰራጨት የሚታወቅ የኦን ላይን መፅሄት ነው፡፡
ራነርስ ወርልድ ባሰፈረው ፅሁፍ ላይ አክሎም ታላቁ ሩጫ ላይ በተሳታፊነት የሚታዮ አትሌቶች በተወዳደሩበት አመት የማይታወቁ ቢሆኑም በ5 አመት ጊዜ ውስጥ በአለም አቀፍ ደረጃ ሁሉም በየቤቱ የሚያነሳቸው ታዋቂ አትሌቶች ይሆናሉ ሲልም አክሏል፡፡
22ተኛው ዙር የ2015 ቶታልኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ህዳር 11 ቀን 2015 ዓ.ም. ይካሄዳል፡፡