ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የ 22ኛ ዙር ውድድር 40ሺ የመሮጫ ቦታዎች ውስጥ ግማሹን አገባደደ፡፡

Share This Post

Share on facebook
Share on linkedin
Share on twitter
Share on email

ከተለያዩ ሃገራት የሚመጡ ተሳታፊዎችን ለማስተናገድ እየተዘጋጀ ያለው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የ 22ኛ ዙር ውድድር 40ሺ የመሮጫ ቦታዎች ውስጥ ግማሹን አገባደደ፡፡

የ2015 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለምአቀፍ 10ኪ.ሜ. ለ22ኛ ጊዜ ሊካሄድ ዝግጅት ተጀምሯል፡፡ትምህርት ለሁሉም ህፃናት የዘንድሮ የሩጫ መልዕክት ነው፡፡ዘንድሮ 40ሺ ተሳታፊዎች የሚሳተፉ ሲሆን ይህ ቁጥር ባለፉት 2 አመታት በነበረው ወረርሽኝ ምክንያት ቀንሶ የነበረውን ተሳታፊ ቁጥር ከፍ እንዲል ያደርገዋል፡፡


የ22ኛው ዙር ሩጫ ምዝገባ በተጀመረ 4 ቀናት ውስጥ 20ሺ ቦታዎች ተሽጠዋል፡፡ በቀጣይ 4 ቀናት ውስጥ ምዝገባ ለማገባበድ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከምዝገባ አጋሮቹ አሞሌና ዳሽን ባንክ ጋር ተዘጋጅቶ ይጠብቃል፡፡ ውድድሩ 3 የተለያዩ የመነሻ ማዕበል አይነቶች ሲኖሩት፤ አረንጓዴ ማዕበል ሰአታቸውን ለማሻሻል ለሚሮጡ የሚመከር፡፡ ቢጫ ለሚዝናኑ፤ ለሚጨፍሩና በርከት ብለው ለሚሮጡ የሚመረጥ፡፡ ቀይ በራሳቸው ፍጥነት ተረጋግተው ለሚሮጡ፤ ዱብ ዱብ ለሚሉ ተወዳዳሪዎች የተዘጋጁ ናቸው፡፡

ሩጫው ህዳር 11 ቀን 2015 ዓ.ም ይካሄዳል።

More To Explore

10KM

የ2015 ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ ዘመቻ የታቀደለትን ገቢ አሰባስቦ ለሶስት በጎ አድራጎት ድርጅቶች አስረከበ፡፡

በዘመቻው ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በተለያዩ መንገዶች ተሰብስቧል፡፡ ታህሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም.፡- ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ቢሮ ጋር በመተባበር የተለያዩ