ሰኔ 4 ቀን 2013 ዓ.ም.
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግል ማህበር ዛሬ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ጥቁር ማልት ከሆነው እና ሙሉ በሙሉ ከተፈጥሮ ንጥረ- ነገሮች ከተሰራው ሶፊ ማልት ጋር የብራንድ አጋርነት ውል ተፈራረመ፡፡ የብራንድ አጋርነት ውል ፍርርሙ የተካሄደው ለ8 ሳምንታት በተካሄደው ለወርቅ ይነሱ ሩጫ ፕሮግራም ማጠናቀቂያ ላይ ነው፡፡
ይህ የብራንድ አጋርነት ፊርማ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በዓመት ውስጥ የሚያካሂዳቸውን ዋና ዋና ሩጫዎች ማለትም ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ- ህዳር ላይ የሚደረገው 10ኪሜ ኢንተርናሽናል ሩጫ፤ የካቲት ወር ላይ የሚካሄደው የሃዋሳው ግማሽ ማራቶን እና የመጋቢቱ ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ ሩጫን የሚሸፍን ሲሆን ሶፊ ማልት ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር ከዚህ ቀደም በቅድሚያ ለሴቶች ሩጫ ስያሜ ስፖንሰርነትና የዛሬውን በጫካ ይሩጡ-ለወርቅ ይነሱ ሩጫን በብቸኛ አጋርነት በማዘጋጀት የጎለበተ ግንኙነት እንዳለው ይታወቃል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ እንደሚታወሰው ሶፊ ማልት ባለፈው ዓመት በአይነቱ ለየት ያለውን ከኮቪድ 19 የቨርቱዋል ሩጫ በአጋርነት ሰርቷል፡፡ የብራንድ አጋርነት ጊዜው እስከ 2015 አ.ም. አጋማሽ የሚቆይ ይሆናል፡፡
ፍቃዱ በሻህ – የሶፊ ማልት የኤክስተርናል ሪሌሽንስ እና ሰስቴነቢሊቲ ማናጀር በዝግጅቱ ላይ እንደተናገሩት ፤ ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር ቀድመን የጀመርነውን ግንኙነት ወደ ብራንድ አጋርነት በመቀየራችን በጣም ደስተኞች ነን፤ በቀጣይ ወራትም ጤናማነት እና ብቁ የህበረተሰብ በመፍጠር ስራ ላይ የተሻለ ለውጥ ለማምጣት መስራታችንን የምንቀጥል ይሆናል፡፡
የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ማርኬቲንግ ዳይሬክተር የሆነችው ህሊና ንጉሴ ከሶፊ ማልት ጋር በአጋርነት መስራት መቻላችን በጣም ጥሩ አጋጣሚ ነው፡፡ ምክንያቱም ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ብዙ ሩጫን የሚያዘወትሩ የማህበረሰብ ክፍሎችን ማብዛት ራእዩ አርጎ እየሰራበት ስለሆነ እና ሶፊ ማልትም ጤናማ አኗኗርን የሚያበረታታ በመሆኑ ለሁለታችንም ጥሩ አይነት አጋጣሚ ነው፡፡ በማለት አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ እና የሶፊ ማልት አጋርነት የተፈጥሮ ጤና በአንድነት በሚል የሚገለጥ እንደሆነም በፍርርሙ ወቅት ታውቋል፡፡
ስለታላቁ ሩጫ የበለጠ ለማወቅ www.ethiopianrun.org ለበለጠ መረጃ፡ ሕሊና ንጉሴ፣ 0911601710 የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ማርኬቲንግ ዳይሬክተር
ኢሜል ፡- hilina@ethiopianrun.org