ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ “ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ” በሚል ፕሮግራሙ ያሰባሰበውን የ1.8 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለአራት በጎ አድራጊ ድርጅቶች አበረከተ::

Share This Post

Share on facebook
Share on linkedin
Share on twitter
Share on email

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ “ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ” በሚል ፕሮግራሙ ያሰባሰበውን የ1.8 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለአራት በጎ አድራጊ ድርጅቶች አበረከተ::

ኃይለእግዚአብሔር አድሐኖም – ታህሳስ 11/2011 ዓ.ም

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከዚህ በፊት በነበሩት አመታት እንደሚያደርገው ሁሉ፡ ከሚያከናውነው አመታዊ የታላቁ ሩጫ የ10ኪ.ሜ የጎዳና ላይ የአትሌቲክስ ውድድር ጎን ለጎን የበጎ አድራጎት ስራ የሚያከናውኑ ድርጅቶችን በገንዘብ ለማገዝ፡ ‘ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ’ በሚል መርህ፡ ከተለያዩ ድርጅቶች እና አላማውን ከሚደግፉ ግለሰቦች ያሰባሰበውን የ1.8 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ ለአራት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች በዛሬው እለት አበርክቷል፡፡

ስለ እናት ማህበር፡ ጆይፉል ላይፍ፡ የአዲስ አበባ ሴቶች ማህበር እና የኢትዮጵያ ስኳር ህሙማን ማህበር፡ የተሰኙት ተቋማት ባቀረቡት ፕሮፖዛል ምክንያት ተመርጠው ለእያንዳንዳቸው የ450,000 ብር የገንዘብ ድጋፍ የተደረገላቸው ድርጅቶች ናቸው፡፡

ቫቲካን ኢምባሲ አካባቢ በሚገኘው ስለ እናት ማህበር በተከናወነው የድጋፍ ርክክብ ፕሮግራም ላይ፡ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የቦርድ ሰብሳቢ ኃይሌ ገብረስላሴ፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሴቶች እና ህጻናት ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሜሮን አራጋው እንዲሁም ድጋፍ የተደረገላቸው ተቋማት አምባሳደር የሆኑ አርቲስቶች እና የተቋማቱ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በዚህ የድጋፍ ርክክብ እና ገቢውን በማሰባሰብ ሂደቱ ወቅት አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት እውቅና የመስጠት ስነስርአት ላይ፡ ” ለሀገር መስራት፡ የተቸገሩ ወገኖችን በራስ አቅም ማገዝ እና ዛሬ ድጋፍ የተደረገላቸውንም ሆነ ሌሎች የበጎ አድራጊ ተቋማትን አቅም በፈቀደ ሁሉ ማገዝ” የሁሉም ኢትዮጵያዊ ሀገራዊ የዜግነት ግዴታ መሆኑን የተለያዩ አካላት አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በዚህ ፕሮጀክቱ ስም እስከ አሁን ድረስ 13.3 ሚሊዮን ብሮችን ከለጋሽ አካላት በማሰባሰብ ለ40 ግብረሰናይ ድርጅቶች ድጋፍ ማድረጉም በእለቱ ተገልጿል፡፡

More To Explore

10KM

የ2015 ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ ዘመቻ የታቀደለትን ገቢ አሰባስቦ ለሶስት በጎ አድራጎት ድርጅቶች አስረከበ፡፡

በዘመቻው ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በተለያዩ መንገዶች ተሰብስቧል፡፡ ታህሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም.፡- ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ቢሮ ጋር በመተባበር የተለያዩ