ሶፊ ማልት በአፍሪካ ትልቁ የሆነውን የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ስያሜ ወሰደ

Share This Post

Share on facebook
Share on linkedin
Share on twitter
Share on email

ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም.

የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አዘጋጆች ህዳር 11 ቀን 2015 ዓ.ም. ለ22ኛ ጊዜ ለሚያካሂዱት ውድድር የስያሜ ስፖንሰር ሶፊ ማልት መሆኑን አሳውቀዋል፡፡ ሄኒከን ኢትዮጵያ በሶፊ ማልት ምርቱ ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር ከዚህም በተጨማሪ የተለያዩ ውድድሮች ላይ በአጋርነት ይሰራል፡፡

ሳምራዊት ግርማ የሄኒከን ስፖንሰርሽፕ እና ብራንድ ማናጀር የዚህ ስምምነት መጠናቀቅን አስመልክተው “በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሚዘጋጁ ውድድሮችን በጣም እንወዳቸዋለን፤ ደረጃቸውን የጠበቁና የብዙ አመት የስራ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች መገንባታቸው የሚመሰገን ሲሆን በተጨማሪም ማህበረሰቡ ጋር ለመድረስ መትጋታቸውና ሰዎች ጤናማና ንቁ አኗኗርን ዘይቤአቸው እንዲያረጉ መስራታቸው ከሶፊ ማልት ምርት የጤና እና ምግብ ንጥረ ነገር ጥቅም ጋር አብሮ ይሄዳል’’ ብለዋል፡፡

ሶፊ ማልት በኢትዮጵያ ላለፉት 5 አመታት የስፖርት ኢንደስትሪ ውስጥ በንቃት ተሳታፊ በመሆን ይንቀሳቀሳል፡፡ ለዚህም ተጠቃሽ የሚሆነው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን የረጅም ጊዜ አጋር እንዲሁም የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አመታዊ ሩጫ የሆነው ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. የስያሜ አጋርም ሆኖ ሰርቷል፡፡ ሶፊ ማልት በአይነቱ ለየት ያለ የብራንድ አጋርነት ውልም ከታላቁ ሩጫ ጋር ተፈራርሞ በጋራ እየሰራ ይገኛል፡፡

የኔዘርላንድ አምባሳደር የሆኑት ሄንክ ጃን ባከር “ትልልቅ ከሚባሉት የደች ድርጅቶች ውስጥ አንዱ የሆነው ድርጅት እና በግሌ በጣም ከማደንቃቸው ውድድሮች አንዱ የሆነው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በአጋርነት መስራታቸው ለሃገሪቱ ስፖርት እና ለማህበረሰብ መነቃቃት የሚጨምረው የላቀ አስተዋፅኦ ይኖራል” በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መስራች አትሌት ሀይሌ ገ/ስላሴ “’ሶፊ ማልት ከታላቁ ሩጫ ራዕይ ጋር በጣም ተያያዥነት አለው፤ አብሮም ይሄዳል ብዙ ሰዎችንም ወደ ሩጫና ብቁ የማህበረሰብ አካል ከማድረግ አንፃር ብዙ መስራት ይቻላል’’ ብሏል፡፡ ይህንንም ሃሳብ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ ሲያጠናክሩ ’’ሶፊ ማልት እንደስያሜ ስፖንሰር ሆኖ መምጣቱ ከዚህ ቀደም የነበረንን ግንኙነት ያጠናክራል፡፡ በመሆኑም አዳዲስ ሃሳቦችን የጨመርን በጋራ አለም አቀፉን 10ኪ.ሜ. ውድድር ወደተሻለ ደረጃ ለመውሰድ እንድንሰራ ይረዳናል፡፡’’

የ2015 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጰያ አለምአቀፍ 10ኪ.ሜ. ውድድር ይፋዊ መክፈቻ የፊታችን ሃምሌ 8 ቀን 2014ዓ.ም. ይካሄዳል፡፡ የውድድሩ ምዝገባ ቀንና ተያያዥ መረጃዎች በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የሚሰጡ ይሆናል፡፡

ለበለጠ መረጃ ሕሊና ንጉሴ 0911601710 ወይም hilina@ethiopianrun.org

More To Explore

10KM

የ2015 ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ ዘመቻ የታቀደለትን ገቢ አሰባስቦ ለሶስት በጎ አድራጎት ድርጅቶች አስረከበ፡፡

በዘመቻው ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በተለያዩ መንገዶች ተሰብስቧል፡፡ ታህሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም.፡- ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ቢሮ ጋር በመተባበር የተለያዩ