ጥር 26 ቀን 2014 ዓ.ም.፡- የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አዘጋጆች ሳፋሪኮም ቴሌኮሚኒኬሽን ኢትዮጵያ መጋቢት 4 ቀን የሚካሄደውን የቅድሚያ ለሴቶች 5ኪሜ ሩጫ በስያሜ ስፖንሰርነት ይሰራ እንደሆነ ታወቀ፡፡
የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅ የሆኑት ዳግማዊት አማረ የ19ነኛው ዙር የቅድሚያ ለሴቶች 5ኪሜ ሩጫን ስፖርትና ወጣቶች ላይ ከሚሰሩ ጋር በመተባበር በተለይ አተኩሮ በመስራት ከሚታወቀው ሳፋሪኮም ጋር በአጋርነት ለመስራት በመቻላችን ደስታ ይሰማናል፡፡ ደረጃውን የጠበቀ ውድድሮችን በማቅረብ የሚታወቀውና ከተለያየ የእድሜ ክልል፤ የገቢ ደረጃና አኗኗር የሚመጡ ተሳታፊዎችን የሚያሳትፍ ውድድር የሚያዘጋጀው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያም ከሳፋሪኮም ጋር በአጋርነት መስራቱም መልካም አጋጣሚ ነው ብለዋል፡፡
ሳፋሪኮም ቴሌኮሚኒኬሽንስ ኢትዮጵያ ባለፈው ሰኔ ወር ኢትዮጵያ ውስጥ ለመስራት ፍቃድ ያገኘ ሲሆን፤ በአፍሪካ ትልቁ የሆነውን የቴሌኮም ኦፕሬሽን በመዘርጋት የካበተ ልምድ ያለው ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ በቀጣይ 10 አመታት የ8.5 ቢልዮን ወጪ በማድግ የመሰረተ ልማት ግንባታ በማድረግ የኢትዮጵያ የዲጅታል ትራንስፎርሜሽን አጀንዳ ለማሳካት ተዘጋጅቷል፡፡
የ2014 ቅድሚያ ለሴቶች ሩጫ ስያሜ ስፖንሰር ሆነን በመስራታችን በጣም ደስተኞች ነን፤ ለወጣቶች የተሻለ እድል በመፍጠር እና የስፖርት ክህሎትን በሃገሪቱ ለማጎልበት በተለያየ መልኩ በማገዝ ለመስራት ተዘጋጅቷል፡፡ በአትሌቲክስ ዘርፍ በምትታወቀው ኢትዮጵያ ኔትወርክ ዝርጋታ ላይ በመስራት ላይ ያለው ሳፋሪኮም ስፖርት የሰዎችን ህይወት ለመለወጥ በተለይም ወጣቶች ላይ ላቅ ያለ ተፅእኖ እንዳለው እናምናለን፡፡ ለዚህም በኢትዮጵያ ውስጥ አትሌቲክስን በማገዝ ሃገር በቀል ችሎታን ለማዳበር መስራት እንፈልጋለን፡፡ ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር አብሮ በመስራቱ ኩራት ይሰማዋል፡፤ ያሉት የሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ሃ/የተ/የግል/ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ አኑዋር ሳውሳ ናቸው፡፡
የዘንድሮው የቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. የምዝገባ መክፈቻ ሰኞ የካቲት 7 ቀን 2014 ዓ.ም. ለ10 ሺ ተሳታፊ ሴቶች ብቻ የሚከፈተ ይሆናል፡፡
ስለ ቅድሚ ለሴቶች 5ኪሜ ሩጫ
ቅድሚ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ለመጀመሪያ ጊዜ ሜይ 16 2004 ተካሄደ፡፡ ይህ ሩጫ ላለፉት 18 አመታት ያለማቋረጥ የተካሄደ ሲሆን በአፍሪካ ትልቁ የሴቶች ብቻ ውድድርም ሆኑዋል፡፡ በ2012 የተካሄደው ይህ ቅድሚያ ለሴቶች ሩጫ 11000 ተሳታፊዎችን ያስተናገደ ሲሆን፤ የውድድሩ ቀንም ማርች 8ን በማስመልከት በመጋቢት ወር ውስጥ ሲካሄድ ቆይቷል፡፡ በዚህ ቅድሚያ ለሴቶች ውድድር ላይ በሚካሄደው የአትሌቶች ውድድር አሸናፊ ከሆኑ አትሌቶች ውስጥ ለመጥቀስ ያህል የ2012 ኦሎምፒክ አሸናፊዋ ቲኪ ገላና፤ 3 ጊዜ ዱባይ ማራቶን አሸናፊዋ አሰለፈች መርጊያ እና የ2021 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አሸናፊ ያለምዘርፍ የኃላው ተጠቃሽ ናቸው፡፡ የዚህ ውድድር አሸናፊ የ16 ዓመቷ ቆንጂት ጥላሁን ነበረች። የኢትዮጵያ ድርብ የኦሎምፒክ ሻምፒዮን መሰረት ደፋር የቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ዉድድር አምባሳደር ነች፡፡