ራእይ አማን እና ሃብታሙ አበራ በአምስተኛው ዙር እንጦጦ ፓርክ ፕሬደተር ሩጫ ለሁለት ተከታታይ ወራት አሸናፊ ሆኑ፡፡

Share This Post

Share on facebook
Share on linkedin
Share on twitter
Share on email

ሰኔ 26 ቀን 2013 ዓ.ም.

የግንቦት ወር አሸናፊ የነበሩት የ13 አመቱዋ ራእይ አማን እና ሃብታሙ አበራ ለሁለተኛ ጊዜ በተከታታይ አሸናፊ ሆነዋል፡፡ ራእይ አማን በ25፡41፡92 ሩጫዋን ከባለፈው ወር ኣሻሽላለች፡፡ ሃብታሙ አበራ በ18፡14፡17 ሩጫውን አሻሽሏል፡፡ በዚሁ እለት ውድድር ላይ በሴቶች አቢጊያ ሰለሞን እና የግሌ እሸቱ በወንዶች ደግሞ አብዱራዛቅ አለዊ እና ምህረት አበራ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሆነው አጠናቀዋል፡፡ በቅዳሜው ውድድር ላይ ከ280 በላይ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን ከእስካሁን ከተደረጉት ውድድሮች ከፍተኛው የተሳታፊ ቁጥር ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

በሚዲያ አባላት መካከል በተደረገው ውድድር ላይ የኢቢኤሱ አብራሃም ክብረአብ አንደኛ ሲሳይ ጌትነት ሁለተኛ እንዲሁም የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬቱ አፈወርቅ አለሙ ሶስተኛ በመውጣት አጠናቀዋል፡፡

ቀጣዩ የእንጦጦ ፓርክ ፕሬደተር ሩጫ ነሃሴ 1 ቀን የሚካሄድ ይሆናል፡፡

More To Explore

10KM

የ2015 ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ ዘመቻ የታቀደለትን ገቢ አሰባስቦ ለሶስት በጎ አድራጎት ድርጅቶች አስረከበ፡፡

በዘመቻው ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በተለያዩ መንገዶች ተሰብስቧል፡፡ ታህሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም.፡- ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ቢሮ ጋር በመተባበር የተለያዩ