“ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ”- ዘንድሮም ጥንካሬውን አሳይቷል

Share This Post

Share on facebook
Share on linkedin
Share on twitter
Share on email

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ “ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ” በሚል መርህ በየዓመቱ ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪሜ ዓለም አቀፍ ውድድሩ ጋር በተያያዘ በሚያከናውነው የበጎ አድራጎት የሚውል የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ የሰራል፡፡ ባለፉት 19 አመታት እሰከ አሁን የተረዱት ሀገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅቶች የዘነደሮውን ጨምሮ 31 ሲሆን በተጨማሪም አምና ዋግምራ ዞን ላይ ትምህርት ቤት በመገንባት ለህብረተሰብ ያሰረከበ ሲሆን በጠቅላላው 15.7 ሚሊየን ብር በላይ ለበጎ ስራ እነዲውል አድርጎል፡፡

በዘንድሮ አመት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ብዙ ድርጅቶች ለእርዳታ የሚሆን በቂ ገንዘብ ባይሰጡም አንዲሁም የታላቁ ሩጫ ተሳታፊዎች ቁጥር በ75% ቢቀንስም 400,000 ብር መሰብሰብ ችሏል፡፡ በየአመቱ እንደሚያደርገውም ኢፌድሪ ሴቶች፤ ህጻናትና ወጣቶች ሚንስቴር ጋር በመተባበር ለተመረጡት እና ከስር ለጠቀስናቸው ሁለት ድርጅቶች ለያንዳንዳቸው 200,000ብር የሚበረከት ይሆናል፡፡

1. ትኩረት ለሴቶችና ለህፃናት ማህበር

2. ኦሞ ቻይልድ ፋውንዴሽን

ትኩረት ለሴቶችና ለህፃናት ማህበር የተጎዱ ሴት እና ህፃናትን የሚረዳ ሲሆን፤ በአሁኑ ሰዓት 31 አካል ጉዳተኛ ህፃናትን በማህበሩ ውስጥ እየረዳ ይገኛል፡፡ የኦሞ ቻይልድ ፋውንዴሽን በሚንጂ ጎጂ ባህላዊ ድርጊቶች ሰለባ ለሆኑ ህፃናት ለመንከባከብና ለማስተማር የተቋቋመ ድርጅት ነው፡፡

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በዛሬው እለት ትኩረት ለሴቶችና ለህፃናት ማህበር ግቢ ውስጥ የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት የገንዘብ ርክክቡን ፈጽሟል፡፡

ለበለጠ መረጃ rebecca@ethiopianrun.org ወይም 0116635757

More To Explore

10KM

የ2015 ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ ዘመቻ የታቀደለትን ገቢ አሰባስቦ ለሶስት በጎ አድራጎት ድርጅቶች አስረከበ፡፡

በዘመቻው ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በተለያዩ መንገዶች ተሰብስቧል፡፡ ታህሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም.፡- ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ቢሮ ጋር በመተባበር የተለያዩ