ለ2014 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5 ኪሜ ውድድር 10,000 ሴቶች ለውድድሩ ተመዘገቡ፡፡

Share This Post

Share on facebook
Share on linkedin
Share on twitter
Share on email

የ2014 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5 ኪሜ ውድድር አዘጋጆች ዛሬ ይፋ እንዳደረጉት የፊታችን እሁድ መጋቢት 13 ቀን 2014 ዓ.ም. ለሚካሄደው ውድድር አስር ሺህ ቲሸርቶች መሸጣቸውን አስታውቀዋል። በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በ2000 ተሳታፊ ብቻ ተወስኖ የነበረው ውድድር ወደ ነበረበት የተሳታፊ መጠን ይመለሳል ::

“ከሁለት አመት በፊት ከደረስንበት የተሳታፊ መጠን ላይ መድረስ በጣም አስደሳች ነው” ሲሉ የተናገሩት የታላቁሩጫ በኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ ዳግማዊት አማረ “ደስታችን ከፍ እንዲል የሚያደርገው ነገር የተሳታፊዎች ቁጥር ብቻ አይደለም ፣ የመንግስትሚኒስትሮች፣ አምባሳደሮች እና ተምሳሌት ሴቶች ከትምህርት ቤት ተማሪዎች እና ከተለያዩ የህይወት መንገድ የሚመጡ ተሳታፊዎችን ማሳተፍውድድሩን ልዩ የሚያደርገው ነው።

ውድድሩ ላይ ከአንድ መቶ በላይ ታዋቂ አትሌቶች የ50,000 ብር ሽልማት አሸናፊ ለመሆን የሚሳተፉ ይሆናል ። በ2012 በፅጌ ገብረሰላማ የተመዘገበው እና ባለፈው አመት በፋንታዬ በላይነህ የተደገመው የ15 ደቂቃ ከ19 ሰከንድ የኮርስ ሪከርድ ለሚሰብርም ተጨመሪ ሽልማት ተዘጋጅቷል ። ሌሎች በቅርቡ ይህን ውድድር ያሸነፉ አትሌቶች ያለምዘርፍ የኋላው እና ፀሃዬ ገመቹ ይገኙበታል ።

በሩጫው የ19-አመት ታሪክ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የአካል ጉዳተኞትውድድርም የሩጫ ፕሮግራሙ አካል ነው። የአውን በጎ አድራጎት ድርጅት መስራች የሆነችው ማርታ ደጀኔ “ በዚህ ዓለም አቀፋዊ ክበብ ውስጥ በሚገኘውና በበርካቶች ዕይታ ውስጥ በሚያልፈው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሚያዘጋጀው ቅድሚያ ለሴቶች 19ኛው ዙር የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ላይ አካል ጉዳተኛ ሴቶችን እንዲህ በልበ ሙሉነት ሲያሳትፍ “ በአንድ ድንጋይ!….” ይሉትን ብሂል በእጅጉ ያጎላዋል ብለዋል፡፡” የሩጫ ውድድር አምባሳደር መሰረት ደፋር እና የታላቁ ሩጫ መስራች ኃይሌ ገብረስላሴ እሁድ ዕለት ይሳተፋሉ።

ማስታወሻ፡ እሑድ መጋቢት 13 ቀን የሚካሄደው የዘንድሮው ውድድር የውድድሩ 19ኛ ዙርነው።ውድድሩቦሌአትላስሆቴልፊትለፊትበሚገኘውበተለመደው ቦታውተጀምሮይጠናቀቃል። ለበለጠመረጃበwww.ethiopianrun.org/en/races/women-first-5km ማግኘትይቻላል።

More To Explore

10KM

የ2015 ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ ዘመቻ የታቀደለትን ገቢ አሰባስቦ ለሶስት በጎ አድራጎት ድርጅቶች አስረከበ፡፡

በዘመቻው ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በተለያዩ መንገዶች ተሰብስቧል፡፡ ታህሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም.፡- ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ቢሮ ጋር በመተባበር የተለያዩ